ለጥያቄዎቻችሁ የተሰጡ ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች!
• ወላጆቼ አስተሳሰቤንና ስሜቴን የማይረዱልኝ ለምንድን ነው?
• አባቴና እናቴ የተለያዩት ለምንድን ነው?
• እውነተኛ ጓደኞች ላፈራ የምችለው እንዴት ነው?
• በጣም የምጨነቀው ለምንድን ነው?
• ልጆቹ የሚያስቸግሩኝ ለምንድን ነው?
• ከጋብቻ በፊት የጾታ ግንኙነት ቢፈጸም ምናለበት?
ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የተባለው መጽሐፍ ለወጣቶች ተብለው ከሚዘጋጁት ሌሎች መጻሕፍት የተለየ ነው። ይህ መጽሐፍ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በርካታ ወጣቶችን በማነጋገርና አስተያየታቸውን በማሰባሰብ የተዘጋጀ ነው። በተጨማሪም መጽሐፉ የሚሰጣቸው በአምላክ ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ መልሶች ተግባራዊ መሆን የሚችሉ ናቸው! ከላይ ያሉት ጥያቄዎች ይህ ባለ 320 ገጽ መጽሐፍ ከሚመልሳቸው ጥያቄዎች መካከል ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው።
አንተም ይህን መጽሐፍ ማግኘት የምትፈልግ ከሆነ ቅጹን ሞልተህ በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ትችላለህ።
□ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።