የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g03 9/8 ገጽ 32
  • ለወጣቶች የተዘጋጀ መጽሐፍ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለወጣቶች የተዘጋጀ መጽሐፍ
  • ንቁ!—2003
ንቁ!—2003
g03 9/8 ገጽ 32

ለወጣቶች የተዘጋጀ መጽሐፍ

በአርካንጂልስክ በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ የምትማር አንዲት ተማሪ በሩሲያ ላለው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ ደብዳቤ ጽፋ ነበር። አንድ ሰው መንገድ ላይ በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀ መጽሔት እንደሰጣት ገልጻ እንዲህ ብላለች:- “መጽሔቱ ስለ ሕይወት እንዲሁም ስለ አምላክና ስለ ሃይማኖት እንዳስብ አድርጎኛል። መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት እፈልጋለሁ። ማናችንንም ሳያውቀን ሕይወቱን በመስጠት ኃጢአታችንን ስላስተሰረየልንና መዳንን ስላስገኘልን ሰው ተጨማሪ እውቀት ማግኘት እፈልጋለሁ።”

አክላም እንዲህ ብላለች:- “የምታከናውኑት ሥራ በተለይ ልጆች ክፉውን ከደጉ መለየት እንዲችሉ ለመርዳት የምታደርጉት ጥረት በጣም አስፈላጊ ነው። ልጆች ልክ እንደ ስፖንጅ በዙሪያቸው ያለውን የሚመጥጡ ከመሆኑም በላይ አካባቢያቸውን ለመምሰል ለውጥ ያደርጋሉ።” ተማሪዋ ታናናሾቿ የሆኑ ወንድምና እህት ስላሏት ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የተባለው መጽሐፍ እንዲላክላት ጠይቃለች። “መጽሐፉ ለትምህርት ቤትም ሆነ ለአጠቃላይ ሕይወታቸው ይጠቅማቸዋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ” ብላለች።

አንተም ወጣቶች በጊዜያችን የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች እንዲወጡ ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀውን ይህን መጽሐፍ ማግኘት ትችላለህ። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተህ በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ የዚህን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ማግኘት ትችላለህ።

□ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ