የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g03 10/8 ገጽ 32
  • “ሁሉም ሰው ሊያነብበው ይገባል”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ሁሉም ሰው ሊያነብበው ይገባል”
  • ንቁ!—2003
ንቁ!—2003
g03 10/8 ገጽ 32

“ሁሉም ሰው ሊያነብበው ይገባል”

በካሊፎርኒያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የሚኖር አንድ ሰው ወደ ይሖዋ ቅረቡ (እንግሊዝኛ) የተባለውን መጽሐፍ የገለጸው ከላይ ባለው መንገድ ነው። “መጽሐፉ ለማንበብ የሚጋብዝ፣ ማራኪ ሥዕላዊ መግለጫዎች ያሉትና በርካታ መንፈሳዊ እንቁዎች የያዘ ነው” ሲል ጽፏል። ከዚያም “ድንቅ ስለ ሆነው አምላካችን የሚገልጽ እንደዚህ ዓይነት ግሩም መጽሐፍ ስላዘጋጃችሁ በጣም አመሰግናችኋለሁ” በማለት ደምድሟል።

ሌሎችም እንደሚከተለው ያሉ ተመሳሳይ አስተያየቶች ሰጥተዋል:- “መጽሐፉን ከዳር እስከ ዳር አንብቤዋለሁ። በጣም ስለወደድኩት አንብቤው ስጨርስ ትንሽ ቅር ብሎኛል። ደግነቱ በጥንቃቄ እያጠናሁትና በጥልቅ እያሰላሰልኩበት እንደገና ላነብበው አስቤያለሁ።”

አንዲት ሌላ ሴት ደግሞ እንዲህ ብላለች:- “ስለ አምላካችን ርኅራኄና ይቅር ባይ ስለመሆኑ የቀረቡት ሐሳቦች በጥልቅ የነኩኝ ከመሆኑም በላይ ወደ አባታችንና ሕይወት ሰጪያችን ይበልጥ እንደቀረብኩ ሆኖ እንዲሰማኝ አድርገውኛል።”

እርስዎም ይህንን መጽሐፍ ቢያነብቡ በሰማይ ወደሚኖረው አባታችን ወደ ይሖዋ ይበልጥ እንደሚቀርቡ እናምናለን። መጽሐፉ “ታላቅ ኃይል ያለው፣” “ፍትህን ይወዳል፣” “ልቡ ጠቢብ ነው” እንዲሁም “እግዚአብሔር ፍቅር ነው” የሚሉ አራት ክፍሎች አሉት። የአምላክ ዋና ዋና ባሕርያት ከተብራሩባቸው ከእነዚህ ክፍሎች በፊት ሦስት የመግቢያ ምዕራፎች አሉ። ይህ 31 ምዕራፎች ያሉት መጽሐፍ “ወደ ይሖዋ ቅረቡ፤ ወደ እናንተም ይቀርባል” በሚለው ምዕራፍ ይደመደማል።

ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህን ስስ ሽፋን ያለው ባለ 320 ገጽ መጽሐፍ ማግኘት ይችላሉ።

□ ወደ ይሖዋ ቅረቡ የተባለውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ