የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 4/07 ገጽ 32
  • “ግሩም የማስተማሪያ መሣሪያ!”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ግሩም የማስተማሪያ መሣሪያ!”
  • ንቁ!—2007
ንቁ!—2007
g 4/07 ገጽ 32

“ግሩም የማስተማሪያ መሣሪያ!”

በአሁኑ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን ለማስጠናት በሰፊው ጥቅም ላይ እየዋለ ያለውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ አስመልክቶ ከላይ ያለውን ሐሳብ የጻፈው በፓናማ የሚኖርና የሙሉ ጊዜ አገልጋይ የሆነ አንድ የይሖዋ ምሥክር ነው። መጽሐፉ 224 ገጾች ያሉት ሲሆን ውብ የሆኑ ሥዕሎችን አካትቷል። ይህ የይሖዋ ምሥክር አክሎ እንዲህ በማለት ጽፏል:- “ሐሳቦቹ በሚያስገርም ሁኔታ እጥር ምጥን ያሉ፣ ተያያዥነት ያላቸውና አሳማኝ በሆነ መንገድ የቀረቡ ናቸው። ተጨማሪው ክፍልና የማመሳከሪያ ጽሑፎቹ የቀረቡበት መንገድ አንባቢው ወዲያውኑ ተጨማሪ ምርምር እንዲያደርግ የሚያነሳሱ ናቸው።”

በሚዙሪ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር አንዲት የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ “መጽሐፉ ቀለል ባለ መንገድ የተጻፈ መሆኑ አስደስቶኛል። ርዕሰ ትምህርቶቹ የቀረቡት ምክንያታዊ በሆነ ቅደም ተከተል መሆኑ ከሌሎቹ ልዩ አድርጎታል” በማለት ጽፋለች። ይህች አስተማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለው መጽሐፍ እንደወጣ ወዲያውኑ ከዚህ በፊት መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ጀምራ ከብዷት ላቋረጠች አንዲት ሴት ወሰደችላት።

አስተማሪዋ እንዲህ ብላለች:- “መጽሐፉን እንደወደደችው ደውላ ስትነግረኝ ገና የመጀመሪያውን ምዕራፍ እንኳ አንብባ አልጨረሰችም ነበር።” ይህች ጥናት መጽሐፉ ለእርሷ እንደተጻፈ ያህል ሆኖ እንደሚሰማት የተናገረች ሲሆን ጥናቷንም እንደገና መቀጠል ፈልጋለች። የመጀመሪያዎቹን አሥር ምዕራፎች አጥንተው ከጨረሱ በኋላ ተማሪዋ በምታጠናው ነገር መደሰቷ ከልብ እንዳስፈነደቃት አስተማሪዋ ተናግራለች።

የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለው መጽሐፍ ከወጣ ሁለት ዓመት ያልሞላው ቢሆንም እስካሁን ከ150 በሚበልጡ ቋንቋዎች ታትሞ ከ50 ሚሊዮን በላይ በሚሆኑ ቅጂዎች ተሰራጭቷል። ይህን መጽሐፍ ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች ውስጥ አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ