የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 2/10 ገጽ 3
  • “በቃኝ፣ መገላገል እፈልጋለሁ!”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “በቃኝ፣ መገላገል እፈልጋለሁ!”
  • ንቁ!—2010
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጋብቻ ማዕበሉን መቋቋም ይችል ይሆን?
    ንቁ!—2006
  • ፍቅር በጠፋበት ትዳር ተጠምዶ መኖር
    ንቁ!—2001
  • መፍትሄው መፋታት ነው?
    ንቁ!—2004
  • ለሁለት የተከፈለ ቤት—መፋታት በወጣቶች ላይ የሚያስከትለው ችግር
    ንቁ!—2009
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2010
g 2/10 ገጽ 3

“በቃኝ፣ መገላገል እፈልጋለሁ!”

ቤቱ ውድቅድቅ ያለ መሆኑ ለረጅም ጊዜ ችላ እንደተባለ ያስታውቃል። ባለፉት ዓመታት በተደጋጋሚ በውሽንፍር የተመታ ሲሆን በአንዳንዶቹ ወቅቶች ከባድ ጉዳት ደርሶበታል። አሁን ግን ምሰሶው ስለተናጋ ቤቱ መፍረሱ የማይቀር ይመስላል።

ይህ ምሳሌ በዛሬው ጊዜ ብዙ ትዳሮች የሚገኙበትን ሁኔታ ጥሩ አድርጎ ይገልጻል። እናንተስ ትዳራችሁ ወደዚህ አቅጣጫ እያመራ እንደሆነ ይሰማችኋል? ከሆነ ችግር የማያጋጥመው ትዳር እንደሌለ እርግጠኛ ሁኑ። እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ የሚያገቡ ሰዎች “በሥጋቸው ላይ መከራ ይደርስባቸዋል” በማለት እውነታውን በግልጽ አስቀምጦታል።—1 ቆሮንቶስ 7:28

አንድ የተመራማሪዎች ቡድን የሰጠው ሐሳብ የዚህን ጥቅስ እውነተኝነት ያጠናክራል፤ ጋብቻ “በማኅበረሰባችን ውስጥ አብዛኞቹ ሰዎች በተለምዶ የሚወስዱት በጣም አደገኛ እርምጃ” እንደሆነ ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል። አክለውም እንዲህ ብለዋል፦ “በጣም አስደሳች የነበረውና በብሩህ ተስፋ የተጀመረው ግንኙነት አንድ ሰው በሕይወቱ ውስጥ ካጋጠሙት ሁሉ የከፋ ሥቃይና ብስጭት የሚያስከትልበት ሊሆን ይችላል።”

የእናንተስ ትዳር? ከታች ከተዘረዘሩት ችግሮች ቢያንስ አንዱ ትዳራችሁን እየበጠበጠው ነው?

  • የማያባራ ጭቅጭቅ

  • መራራ ንግግር

  • ውስልትና

  • ቅሬታና ምሬት

ትዳራችሁ እንደተናጋና ሊፈርስ እንደተቃረበ የሚሰማችሁ ከሆነ ምን ማድረግ ይኖርባችኋል? መፍትሔው መፋታት ነው?

“እንግዳ ነገር መሆኑ ቀርቶ የተለመደ ክንውን ሆኗል”

በአንዳንድ አገሮች ፍቺ በከፍተኛ ፍጥነት ጨምሯል። ለበርካታ ዓመታት ፍቺ ያልተለመደ ነገር በነበረበት በዩናይትድ ስቴትስ ያለውን ሁኔታ እንመልከት። ባርብራ ደፎ ኋይትሄድ ዘ ዲቮርስ ካልቸር በተባለው መጽሐፋቸው ላይ እንደገለጹት ከ1960 በኋላ ፍቺ “በጣም አስደንጋጭ በሆነ ፍጥነት ጨምሯል።” አክለው እንዲህ ብለዋል፦ “ወደ አሥር ዓመት በሚጠጋ ጊዜ ውስጥ የፍቺ ቁጥር በእጥፍ ያደገ ሲሆን እስከ 1980ዎቹ መጀመሪያ ዓመታት ባለው ጊዜ ማሻቀቡን ቀጠለ፤ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ በዚህች አገር የነበረው የፍቺ ቁጥር ካደጉ የምዕራባውያን አገሮች መካከል ከፍተኛው ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር። የፍቺ ቁጥር በጣም ፈጣንና ቀጣይ በሆነ መንገድ በመጨመሩ በሦስት አሥርተ ዓመታት ውስጥ ብቻ ፍቺ በአሜሪካውያን ሕይወት ውስጥ እንግዳ ነገር መሆኑ ቀርቶ የተለመደ ክንውን ሆኗል።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ