በትምህርትህ ስኬታማ መሆን እንድትችል የሚረዱ መጻሕፍት
● በክፍል ውስጥ የሚያጋጥሙኝን ውጥረት የሚፈጥሩ ሁኔታዎች መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?
● የፈተና ውጤቴን ማሻሻል የምችለው እንዴት ነው?
● ከአስተማሪዬ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖረኝ ማድረግ የምችለው እንዴት ነው?
● ግቦቼ ላይ መድረስ የምችለው እንዴት ነው?
ከላይ የተጠቀሱትን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ርዕሶችን ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች በተባለው መጽሐፍ ጥራዝ 1 እና ጥራዝ 2 ላይ ማግኘት ይቻላል።
በተጨማሪም በእነዚህ መጻሕፍት ላይ ጓደኝነትን፣ ስሜትን እንዲሁም ከተቃራኒ ፆታ ጋር የሚመሠረት ጓደኝነትን አስመልክቶ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ምክር ማግኘት ትችላለህ።
ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተህ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ መጽሐፎቹን ማግኘት ትችላለህ።
□ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች፣ ጥራዝ 1 የተባለውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ላኩልኝ።
□ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች፣ ጥራዝ 2 የተባለውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።