ልጆች ከወላጆቻቸው የሚፈልጉት ነገር
በዛሬው ጊዜ፣ ልጆች ለዓመፅና ሥነ ምግባርን ለሚሸረሽሩ ድርጊቶች በጣም ተጋልጠዋል። በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ ትናንሽ ልጆች ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ በሥነ ምግባር ረገድ መለኮታዊ አመራር ያስፈልጋቸዋል። ታዲያ ወላጆች ልጆቻቸውን በማሠልጠን ረገድ ምን ሊረዳቸው ይችላል? በርካታ ወላጆች፣ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው አመራርና የያዛቸው የሥነ ምግባር ደንቦች ጊዜ የማይሽራቸው እንደሆኑ ስለሚያምኑ በዚህ ረገድ የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያ ለመከተል መርጠዋል።
ወላጆች ልጆቻቸውን በማሠልጠን ረገድ እንዲሳካላቸው ለመርዳት፣ የይሖዋ ምሥክሮች ከታላቁ አስተማሪ ተማር የተባለውን መጽሐፍ አዘጋጅተዋል። መጽሐፉ ውስጥ ከሚገኙት 48 ምዕራፎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦ “ታዛዥነት ይጠብቅሃል፣” “ይቅር ማለት ያለብን ለምንድን ነው?” “መዋሸት የሌለብን ለምንድን ነው?” “ያለብንን ፍርሃት ለማሸነፍ የሚያስችል እርዳታ” እንዲሁም “ሥራ መሥራት የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?”