የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 4/13 ገጽ 12-13
  • ኢንዶኔዥያን እንጎብኝ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢንዶኔዥያን እንጎብኝ
  • ንቁ!—2013
ንቁ!—2013
g 4/13 ገጽ 12-13

አገሮችና ሕዝቦች

ኢንዶኔዥያን እንጎብኝ

ኢንዶኔዥያ ወደ 17,000 የሚጠጉ ደሴቶችን ያቀፈች አገር ናት። ሕዝቦቿ ልዩ የሆነ ወዳጃዊ መንፈስ የሚንጸባረቅባቸው፣ ትዕግሥተኞች፣ ጨዋዎችና እንግዳ ተቀባዮች ናቸው።

[በገጽ 12 ላይ የሚገኝ ካርታ]

ኢንዶኔዥያውያን አብዛኛው ጊዜ ሩዝን በቅመም ከተሠሩ ሌሎች ምግቦች ጋር የመብላት ልማድ ያላቸው ሲሆን ፍራፍሬዎችንም ይመገባሉ። በኢንዶኔዥያ በአንዳንድ አካባቢዎች ያሉ ቤተሰቦች ምንጣፍ ላይ ተቀምጠው የሚበሉ ሲሆን ሩዙ ላይ ሌሎች ምግቦችን የሚጨምሩት በእጃቸው እየዘገኑ ነው። በርካታ ኢንዶኔዥያውያን ምግቡ በዚህ መንገድ ሲበላ ይበልጥ እንደሚጣፍጥ ይናገራሉ።

የዱሪያን ፍሬ በውስጡ እንደ ክሬም ያለ ፈሳሽ ነገር አለው፤ ኃይለኛ ሽታ ያለው ቢሆንም ብዙዎች ይወዱታል

ኢንዶኔዥያውያን ኪነ ጥበብ፣ ጭፈራና ሙዚቃ ይወዳሉ። አንክሎንግ የኢንዶኔዥያውያን ባሕላዊ የሙዚቃ መሣሪያ ሲሆን በመወጠሪያ ላይ የተንጠለጠሉ ከቀርከሃ የተሠሩ ዘንጎች አሉት። ዘንጎቹ በተገቢው መንገድ ከተስተካከሉ በኋላ ሲነቀነቁ የሚፈለገውን ዓይነት ኖታ ወይም ድምፅ ያወጣሉ። አንድን ዜማ ለመጫወት የሙዚቃ መሣሪያ የሚጫወቱ በርካታ ሰዎች አንድ ላይ ሆነው እያንዳንዳቸው የያዙትን አንክሎንግ በትክክለኛው ጊዜ ይነቀንቁታል።

ኦራንጉተን በሱማትራና በቦርንዮ ባሉት ጥቅጥቅ ያሉ ደኖች ውስጥ በብዛት የሚገኝ ሲሆን በዛፍ ላይ ከሚኖሩ እንስሳት ሁሉ ትልቁ ነው። ትልቁ ተባዕት ኦራንጉተን 90.7 ኪሎ ግራም ሊመዝን ይችላል፤ ክንዶቹ ሲዘረጉ ከጫፍ እስከ ጫፍ 2.4 ሜትር ይሆናሉ

ኢንዶኔዥያ እስከ 15ኛው መቶ ዘመን ዓ.ም. ድረስ ሂንዱይዝምና ቡዲዝም በእጅጉ የተስፋፋባት አገር ነበረች። በ16ኛው መቶ ዘመን እስልምና በኢንዶኔዥያ ማኅበረሰብ ውስጥ ሥር መስደድ ጀመረ። በ16ኛው መቶ ዘመን ቅመማ ቅመም ፈልገው የገቡት አውሮፓውያን የክርስትናን ሃይማኖቶች ይዘው ገቡ።

በዓለም ዙሪያ መጽሐፍ ቅዱስን በማስተማሩ ሥራ የሚታወቁት የይሖዋ ምሥክሮች ከ1931 አንስቶ በኢንዶኔዥያ ውስጥ ሲሰብኩ ቆይተዋል። በዛሬው ጊዜ በኢንዶኔዥያ ከ22,000 በላይ የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ሲሆን መስማት ለተሳናቸው ሰዎች መልእክቱን ለማዳረስ ጥረት እያደረጉ ናቸው። የይሖዋ ምሥክሮች በቅርቡ የኢየሱስ ክርስቶስን ሞት መታሰቢያ ባከበሩበት ወቅት በምልክት ቋንቋ ባካሄዱት ስብሰባ ላይ ከ500 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ተገኝተዋል።

እውቀትህን ፈትሽ

ከሚከተሉት ነገሮች መካከል በኢንዶኔዥያ የሚገኙት የትኞቹ ናቸው?

  1. 20,000 የዕፅዋት ዝርያዎች

  2. ከየትኛውም የምድር ክፍል ይበልጥ በርካታ ዓይነት ያላቸው አጥቢ እንስሳት

  3. የዓለማችን ትልቁ አበባ

  4. የዓለማችን ረጅሙ አበባ

መልስ፦ ሁሉም መልስ ነው። የዓለማችን ትልቁ አበባ 91 ሴንቲ ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን ረጅሙ አበባ ደግሞ 3 ሜትር ከፍታ አለው።

አጭር መረጃ

  • የሕዝብ ብዛት፦ 237,600,000

  • ዋና ከተማ፦ ጃካርታ

  • የአየር ንብረት፦ ሞቃታማ

  • የወጪ ምርት፦ የዘንባባ ዘይት (ፓልም ኦይል)፣ ጎማ፣ ነዳጅ፣ የድንጋይ ከሰል

  • ቋንቋ፦ በኸሳ ኢንዶኔዥያ፣ በአካባቢው የሚነገሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ቋንቋዎችና ቀበሌኛዎች

  • ሃይማኖት፦ አብዛኛው ኅብረተሰብ ሙስሊም (88 በመቶ)

ንቁ! መጽሔት የኢንዶኔዥያ ቋንቋን (በኸሳ ኢንዶኔዥያ ተብሎም ይጠራል) ጨምሮ በ98 ቋንቋዎች ይታተማል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ