የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 10/14 ገጽ 10-11
  • ቤሊዝን እንጎብኝ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቤሊዝን እንጎብኝ
  • ንቁ!—2014
ንቁ!—2014
g 10/14 ገጽ 10-11
የቤሊዝ የባሕር ዳርቻ

አገሮችና ሕዝቦች

ቤሊዝን እንጎብኝ

የቤሊዝ ካርታ

ቤሊዝ ትንሽ አገር ብትሆንም የተለያዩ መልክዓ ምድሮችን የያዘች አገር ናት፤ ሞቃታማና እርጥበታማ የአየር ንብረት ባለው አካባቢ የሚገኙት ዓይነት ደኖች እንዲሁም ሰማያዊ በሆነ ባሕር የተከበቡ በርካታ ደሴቶች በቤሊዝ ይገኛሉ። ይሁንና አገሪቱን አስደናቂ የሚያደርጋት የተለያየ መልክዓ ምድር ያላት መሆኗ ብቻ አይደለም።

በዚህች አገር ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ የእንስሳትና የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ከእነዚህ መካከል ኪል ቢልድ ቱካን የሚባለው በቀለማት ያሸበረቀ ወፍ እንዲሁም ቤርድ ቴፕር የሚባለው እንስሳ ይገኝበታል፤ የአውራሪስ ዝርያ የሆነው ቤርድ ቴፕር የተባለው ይህ እንስሳ አጭር የዝሆን ኩምቢ የሚመስል አፍንጫ ያለው ሲሆን በመሬት ላይም ሆነ በውኃ ውስጥ ውስጥ እንደ ልብ መንቀሳቀስ ይችላል። የኅብረት ኑሮ የማይወዱት የጃጓር ዝርያዎችም በአገሪቱ ይገኛሉ። እንዲያውም ለጃጓሮች የተከለለ ፓርክ የሠራች የመጀመሪያዋ አገር ቤሊዝ ናት።

ጃጓር

ለጃጓሮች የተከለለ ፓርክ የሠራች የመጀመሪያዋ አገር ቤሊዝ ናት

በአንድ ወቅት የማያዎች ግዛት ቤሊዝንም ያጠቃልል ነበር። በ16ኛው መቶ ዘመን የስፔን ወራሪዎች ወደ አካባቢው ቢዘምቱም ማያዎችን ሙሉ በሙሉ ማሸነፍ አልቻሉም። በኋላም እንግሊዝ አካባቢውን የተቆጣጠረች ሲሆን በ1862 ቤሊዝ የብሪትሽ ሆንዱራስ ቅኝ ግዛት መሆኗ ታወጀ። በ1981 ደግሞ ቤሊዝ ነፃነት አገኘች።

ቤሊዝ እንደ መልክዓ ምድሯ ሁሉ ነዋሪዎቿም የተለያዩ ናቸው። በአገሪቱ ውስጥ ካሉት ዋና ዋና ጎሣዎች መካከል ማያ፣ ሜስቲዞ፣ ኢስት ኢንዲያን፣ ክሪኦል እና ጋሪፉና ይገኙበታል። የቤሊዝ ሰዎች ተግባቢና ትሑት ናቸው። ልጆች አዋቂዎችን ሲያናግሩ የአክብሮት መጠሪያዎችን ይጠቀማሉ።

የቤሊዝ ሴቶች በገበያ ቦታ

በቤሊዝ ሲቲ የሚገኝ የገበያ ቦታ

በቤሊዝ ውስጥ በሎው ጀርመን፣ በማንደሪን ቻይንኛ፣ በማያ (ሞፓን)፣ በስፓንኛ፣ በቤሊዝ ክሪኦል፣ በአሜሪካ ምልክት ቋንቋ እና በእንግሊዝኛ የሚካሄዱ የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች አሉ። የይሖዋ ምሥክሮች በ2013 የክርስቶስን ሞት መታሰቢያ ሲያከብሩ በአማካይ ከ40 የቤሊዝ ነዋሪዎች 1ዱ በበዓሉ ላይ ተገኝቷል።

ይህን ታውቅ ነበር? የቤሊዝ ኮራል ሪፍ ከ290 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት አለው። ይህ ኮራል ሪፍ በዓለም ላይ በርዝመቱ ሁለተኛውን ደረጃ የያዘው ኮራል ሪፍ ክፍል ነው። የመጀመሪያውን ደረጃ የያዘው የአውስትራሊያው ግሬት ባሪየር ሪፍ ነው።

የቤሊዝ ኮራል ሪፍ

የቤሊዝ ኮራል ሪፍ በዓለም ላይ በርዝመቱ ሁለተኛውን ደረጃ የያዘው ኮራል ሪፍ ክፍል ነው

አጭር መረጃ

  • የሕዝብ ብዛት፦ 333,000

  • ዋና ከተማ፦ ቤልሞፓን

  • የአስተዳደር ዓይነት፦ ፓርላሜንታዊ ዲሞክራሲ

  • ቋንቋ፦ ስፓንኛ፣ ቤሊዝ ክሪኦል፣ እንግሊዝኛ

  • የአየር ንብረት፦ ሞቃታማ

  • መልክዓ ምድር፦ ተራሮች፣ ደኖች እና ረግረጋማ አካባቢዎች። ጥልቀት በሌለው የውቅያኖስ ውኃ ላይ የሚበቅሉ የማንግሮቭ ዛፎችና በመቶዎች የሚቆጠሩ ደሴቶች ይታያሉ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ