የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 9/15 ገጽ 12-13
  • ኒካራጓን እንጎብኝ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኒካራጓን እንጎብኝ
  • ንቁ!—2015
ንቁ!—2015
g 9/15 ገጽ 12-13
የኦሜቴፔ ደሴት ከኒካራጓ ሐይቅ በፈነዱ እሳተ ገሞራዎች የተፈጠረ ደሴት ነው

የኒካራጓ ሐይቅ ጉልህ ገጽታ ሁለቱን የእሳተ ገሞራ ተራሮች የሚያገናኝ ለም መሬት ያለው የኦሜቴፔ ደሴት ነው

አገሮችና ሕዝቦች

ኒካራጓን እንጎብኝ

የኒካራጓ ካርታ

ብዙ ጊዜ ሰዎች ኒካራጓን የሐይቆችና የእሳተ ገሞራዎች አገር ብለው ይጠሯታል። በመካከለኛው አሜሪካ ከሚገኙት ሐይቆች ሁሉ ትልቅ የሆነው የኒካራጓ ሐይቅ የሚገኘው በዚህች አገር ነው። የአገሬው ተወላጅ የሆኑ ጎሳዎች ኮሲቦካ በማለት የሚጠሩት ሲሆን ትርጉሙም “ጣፋጭ ባሕር” ማለት ነው። ይህ ሐይቅ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደሴቶች ያሉት ሲሆን እንደ ሻርክ፣ ሶርድ ፊሽና ታርፐን የመሳሰሉ ውቅያኖስ ውስጥ የሚኖሩ እንስሳትን የያዘ ብቸኛው ጨዋማ ያልሆነ ሐይቅ ነው።

ሳኩዋንጆቼ የሚባለው የኒካራጓ ብሔራዊ አበባ

ሳኩዋንጆቼ (ፍራንጂፓኒ) የሚባለው የኒካራጓ ብሔራዊ አበባ

በመካከለኛው አሜሪካ በጣም ተገልለው ከሚገኙት አካባቢዎች አንዱ የሆነው የሞስኪቶ የባሕር ጠረፍም የሚገኘው በኒካራጓ ነው። ሥልሳ አምስት ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ይህ ቦታ አብዛኛውን ምሥራቃዊ ዳርቻ ይዞ ጎረቤት አገር እስከሆነችው እስከ ሆንዱራስ ይዘልቃል። የሚስኪቶ ጎሳ (የሞስኪቶ ሌላኛው አጠራር ነው) የኒካራጓ ተወላጅ ከሆኑ በርከት ያሉ ጎሳዎች መካከል አንዱ ሲሆን አውሮፓውያን በ16ኛው መቶ ዘመን ወደዚያ ከመምጣታቸው በፊት አንስቶ ይኖር የነበረ ጎሳ ነው።

ሚስኪቶዎች ጠንካራ ማኅበራዊ ትስስርና ለየት ያለ ባሕል ያላቸው ሕዝቦች ናቸው። ለምሳሌ ያህል፣ በሚስኪቶ ቋንቋ እንደ “አቶ” ወይም “ወይዘሮ” ያሉ የማዕረግ ስሞች አይገኙም። በገጠራማ አካባቢ የሚኖሩ ወጣቶች ዘመዶቻቸው ባይሆኑም እንኳ ታላላቆቻቸውን “አጎቴ” ወይም “አክስቴ” ብለው ይጠሯቸዋል። በሚስኪቶ ጥንታዊ ባሕል መሠረት ሴቶች ከቅርብ ጓደኞቻቸው ወይም ከዘመዶቻቸው ጋር ሰላምታ የሚለዋወጡት ጉንጭና ጉንጫቸውን በማነካካት ነው። ከዚያም ቀድማ ሰላምታ የሰጠችው ሴት በአፍንጫዋ አየር ትስባለች።

የኒካራጓ ተወላጆች

የአገሪቱ ተወላጆች

በማያንኛ እና በሚስኪቶ ቋንቋ የተዘጋጁ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች

በማያንኛ እና በሚስኪቶ ቋንቋ በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጁ መጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ ጽሑፎች

አጭር መረጃ

  • የሕዝብ ብዛት፦ 6,176,000

  • የሥራ ቋንቋ፦ ስፓንኛ። ራስ ገዝ በሆኑ አካባቢዎች ግን እንደ ሚስኪቶ፣ ማያንኛ፣ ራማ እና ክሪኦል እንግሊዝኛ የመሳሰሉ ቋንቋዎች ከስፓንኛ እኩል ይነገራሉ

  • የአስተዳደር ዓይነት፦ ሪፑብሊክ

  • ዋና ከተማ፦ ማናጓ

  • የአየር ንብረት፦ በአብዛኛው ሞቃታማ ቢሆንም ከፍ ባሉ አካባቢዎች ግን ቀዝቀዝ ያለ ነው

  • መልክዓ ምድር፦ በባሕር ዳርቻ የሚገኙት አካባቢዎች ሜዳማ፣ መሃሉ ተራራማ

እውቀትህን ፈትሽ

ስለ ኒካራጓ የሚናገሩትን የሚከተሉትን ዓረፍተ ነገሮች እውነት ወይም ሐሰት ብለህ መልስ፦

  1. ሀ. አገሪቱ ይህን ስያሜ ያገኘችው ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት የጎሳ መሪ ከነበረ ኒካራኦ ከተባለ ሰው ነው።

  2. ለ. ኒካራጓ በስፓኞችም፣ በእንግሊዞችም ቅኝ ግዛት የተያዘች ብቸኛዋ የላቲን አሜሪካ አገር ናት።

  3. ሐ. ባለፉት መቶ ዓመታት፣ ከካሪቢያን የሚመጡ የባሕር ላይ ወንበዴዎች በኒካራጓ ሐይቅ ዳርቻ ያሉ ከተሞችን ይዘርፉ ነበር።

  4. መ. ኒካራጓ በመካከለኛው አሜሪካ ካሉ አገሮች አነስተኛ የሕዝብ ብዛት ያላት አገር ናት።

መልስ፦ ሁሉም እውነት ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ