መግቢያ
በዘመናችን መከባበር ከመጥፋቱ የተነሳ አክብሮት የሚያሳይ ሰው ብርቅ እየሆነ መጥቷል።
ብዙዎች ለሌሎች ሰዎች፣ ለወላጆቻቸው፣ ለአረጋውያን እንዲሁም ለፖሊሶች፣ ለአለቆቻቸውና ለመምህራን አክብሮት የላቸውም። በተጨማሪም ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሰዎች ይሰዳደባሉ። ሃርቫርድ ቢዝነስ ሪቪው ላይ የወጣ አንድ ርዕስ እንደሚገልጸው አክብሮት ማጣት “በእጅጉ እየተስፋፋ ነው።” ብዙ ሰዎች “በተለይ ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ ሁኔታው እየተባባሰ እንደመጣ” ይሰማቸዋል።