የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • my ታሪክ 8
  • በምድር ላይ የነበሩ ግዙፍ ሰዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በምድር ላይ የነበሩ ግዙፍ ሰዎች
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ የተነሳ ዓመፅ
    የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?
  • መላእክት በሕይወታችን ውስጥ ምን ሚና ይጫወታሉ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • መላእክት—“የሕዝብ አገልጋዮች የሆኑ መናፍስት”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ከአምላክ መላእክት የሚገኝ እርዳታ
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
my ታሪክ 8

ምዕራፍ 8

በምድር ላይ የነበሩ ግዙፍ ሰዎች

ከርዝመቱ የተነሳ የቤትህን ጣሪያ ሊነካ የሚችል አንድ ሰው ወዳንተ ሲመጣ ብትመለከት ምን ይሰማህ ነበር? ይህ ሰው በጣም ግዙፍ መሆን አለበት! በአንድ ወቅት በምድር ላይ ግዙፍ ሰዎች ነበሩ። አባቶቻቸው ከሰማይ የወረዱ መላእክት እንደነበሩ መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል። ነገር ግን ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?

ክፉው መልአክ ሰይጣን ችግር ለመፍጠር ይሯሯጥ እንደነበረ አስታውስ። ሌላው ቀርቶ የአምላክ መላእክት ክፉ እንዲሆኑ ለማድረግ ይጥር ነበር። ከጊዜ በኋላ ከእነዚህ መላእክት መካከል አንዳንዶቹ ሰይጣንን መስማት ጀመሩ። አምላክ በሰማይ እንዲሠሩ የሰጣቸውን ሥራ መሥራት አቆሙ። ከዚያ በኋላ ወደ ምድር ወርደው የሰው አካል ለበሱ። ለምን እንደሆነ ታውቃለህ?

እነዚህ የአምላክ ልጆች ይህን ያደረጉት በምድር ላይ የነበሩትን ቆንጆ ሴቶች አይተው ከእነርሱ ጋር ለመኖር ስለ ፈለጉ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ስለዚህ ወደ ምድር መጡና እነዚህን ሴቶች አገቧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ ይህ ድርጊት ትክክል እንዳልሆነ ይናገራል፤ ምክንያቱም አምላክ እነዚህን መላእክት የፈጠራቸው በሰማይ እንዲኖሩ ነው።

እነዚህ መላእክትና ሚስቶቻቸው ልጆች ሲወልዱ የተወለዱት ልጆች የተለዩ ነበሩ። መጀመሪያ እምብዛም ልዩ አልነበሩም ይሆናል። ይሁን እንጂ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደጉና ይበልጥ ጠንካራ እየሆኑ ሄዱና በጣም ግዙፍ ሆኑ።

እነዚህ ግዙፍ ሰዎች ክፉዎች ነበሩ። ግዙፎችና ኃይለኞች ስለ ነበሩ ሰዎችን ያሠቃዩ ነበር። ሁሉም ሰው እንደ እነርሱ ክፉ እንዲሆን ለማስገደድ ይሞክሩ ነበር።

ሄኖክ ቢሞትም እንኳ በምድር ላይ አንድ ጥሩ ሰው ነበር። ይህ ሰው ኖኅ ይባላል። ኖኅ ሁልጊዜ አምላክ ያዘዘውን ያደርግ ነበር።

አምላክ ክፉ ሰዎችን በሙሉ የሚያጠፋበት ጊዜ እንደ ደረሰ ለኖኅ ነገረው። ሆኖም አምላክ ኖኅንና ቤተሰቡን እንዲሁም ብዙ እንስሳትን ከጥፋቱ ለማዳን አስቧል። አምላክ ይህን ያደረገው እንዴት እንደሆነ እስቲ እንመልከት።

ዘፍጥረት 6:​1-8፤ ይሁዳ 6

የአንቀጾቹ ጥያቄዎች

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ