የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • my ታሪክ 74
  • ያለ ፍርሃት ይናገር የነበረው ሰው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ያለ ፍርሃት ይናገር የነበረው ሰው
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኤርምያስ ስለ ይሖዋ መናገሩን አላቆመም
    ልጆቻችሁን አስተምሩ
  • ይሖዋ ኤርምያስን እንዲሰብክ ላከው
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • የኤርምያስ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • እንደ ኤርምያስ ደፋር ሁኑ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
my ታሪክ 74

ምዕራፍ 74

ያለ ፍርሃት ይናገር የነበረው ሰው

ሰዎቹ በዚህ ሰው ላይ ሲያሾፉበት ተመልከት። ይህ ሰው ማን እንደሆነ ታውቃለህ? ኤርምያስ ነው። ኤርምያስ ታላቅ የአምላክ ነቢይ ነው።

ንጉሥ ኢዮስያስ ጣዖታቱን ከምድሪቱ ላይ ማጥፋት ከጀመረ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ይሖዋ ኤርምያስን የእሱ ነቢይ እንዲሆን አዘዘው። ኤርምያስ ግን ልጅ ስለሆንኩ ነቢይ ለመሆን አልችልም ብሎ አስቦ ነበር። ይሁን እንጂ ይሖዋ እንደሚረዳው ነገረው።

ኤርምያስ እስራኤላውያን መጥፎ ነገር መሥራታቸውን እንዲያቆሙ ነገራቸው። ‘አሕዛብ የሚያመልኳቸው አማልክት የሐሰት አማልክት ናቸው’ አላቸው። ሆኖም ብዙዎቹ እስራኤላውያን እውነተኛውን አምላክ ይሖዋን ከማምለክ ይልቅ ጣዖታትን ማምለክ መርጠው ነበር። ኤርምያስ በክፋት ድርጊታቸው የተነሳ አምላክ እንደሚቀጣቸው ሲነግራቸው ይስቁበት ነበር።

ብዙ ዓመታት አለፉ። ኢዮስያስ ሞተና ከሦስት ወራት በኋላ ልጁ ኢዮአቄም ነገሠ። ኤርምያስ ‘መጥፎ ነገር መሥራታችሁን ካላቆማችሁ ኢየሩሳሌም ትጠፋለች’ በማለት ሕዝቡን ማሳሰቡን ቀጠለ። ካህናቱ ኤርምያስን ያዙትና ‘እንዲህ ብለህ በመናገርህ መገደል አለብህ’ ብለው ጮኹ። ከዚያም ለእስራኤል መሳፍንት ‘ኤርምያስ ከተማችን ትጠፋለች ብሎ ስለተናገረ መሞት አለበት’ አሏቸው።

ኤርምያስ ምን ያደርግ ይሆን? ምንም አልፈራም! ሁሉንም እንዲህ አላቸው:- ‘እንዲህ ብዬ እንድናገር የላከኝ ይሖዋ ነው። መጥፎ ነገር መሥራታችሁን ካላቆማችሁ ይሖዋ ኢየሩሳሌምን ያጠፋታል። እኔን ብትገድሉኝ ግን ምንም ጥፋት ያልሠራን ሰው መግደላችሁ እንደሆነ እወቁ።’

መሳፍንቱ ኤርምያስን ተዉት፤ ሆኖም እስራኤላውያን መጥፎ መንገዳቸውን አላስተካከሉም። ከጊዜ በኋላ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መጣና ኢየሩሳሌምን ወረራት። በመጨረሻ ናቡከደነፆር እስራኤላውያንን አገልጋዮቹ አደረጋቸው። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ እስራኤላውያንን ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው። የማታውቃቸው ሰዎች ከአገርህ አውጥተው ወደማታውቀው አገር ቢወስዱህ የሚኖረውን ሁኔታ እስቲ አስበው!

ኤርምያስ 1:​1-8፤ 10:​1-5፤ 26:​1-16፤ 2 ነገሥት 24:​1-17

የአንቀጾቹ ጥያቄዎች

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ