የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • sj ገጽ 3
  • የዚህ ብሮሹር ዓላማ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የዚህ ብሮሹር ዓላማ
  • ትምህርት ቤትና የይሖዋ ምሥክሮች
ትምህርት ቤትና የይሖዋ ምሥክሮች
sj ገጽ 3

የዚህ ብሮሹር ዓላማ

ይህ ብሮሹር የተዘጋጀው በይሖዋ ምሥክሮችና በትምህርት ቤት ባለ ሥልጣኖች መካከል መግባባትና ትብብር እንዲኖር ለመርዳት ነው። በትምህርት ቤት የሚሰጡት መሠረታዊ የትምህርት ፕሮግራሞች እንዲሳኩ ከሚሠሩ ሁሉ ጋር ለመተባበር እንፈልጋለን።

የይሖዋ ምሥክሮች የሆኑ ወላጆች በመማር ማስተማሩ ሂደት አመቺ የሆኑ ሁኔታዎች እንዲኖሩ የበኩላቸውን ድርሻ ለማበርከት ይፈልጋሉ። ልጆቻቸው ከትምህርታቸው የተቻለውን ያህል ብዙ ጥቅም እንዲያገኙ ይፈልጋሉ። ይህንንም ፍላጎታቸውን ለማሳካት አቅማቸው የሚፈቅደውን ሁሉ እንደሚያደርጉ መምህራንና ሌሎች የትምህርት ቤት ባለ ሥልጣኖች እንዲያውቁላቸው ይፈልጋሉ።

የይሖዋ ምሥክሮች በአጠቃላይ፣ የትም ይኑሩ የት፣ በጥሩ ሥነ ምግባራቸው የታወቁ ናቸው። ለመንግሥታዊ ባለ ሥልጣኖችም ታዛዦች በመሆናቸው ታውቀዋል። ሆኖም አንዳንድ መምህራን ምሥክሮች የሆኑ ወጣቶች በሁሉም የትምህርት ቤት ፕሮግራም ወይም ሥራ ስለማይካፈሉ ከትምህርት ቤት ባለ ሥልጣኖችና አስተማሪዎች ጋር ለመተባበር የማይፈልጉ እንደሆኑ ይሰማቸው ይሆናል። ይሁን እንጂ ወጣቶቹ በአንዳንድ ፕሮግራሞችና ሥራዎች ለመካፈል እምቢ የሚሉት ዓመፀኞች ወይም ፀረ–ሕብረተሰብ ስለሆኑ አይደለም። ማንኛውም ተግባራቸው የሚመራው በሃይማኖታዊና በሥነ ምግባራዊ እምነታቸው ነው።

በዚህ ብሮሹር ከትምህርት ቤት እንቅስቃሴዎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸውን የይሖዋ ምሥክሮች እምነቶች ልናስተዋውቃችሁ እንወዳለን። በተጨማሪም ወጣቶቹ ምሥክሮች በእነዚህ እምነቶቻቸው ምክንያት በዓለም ዙሪያ በብዙ ቦታዎች የተለመዱ በሆኑት አንዳንድ የትምህርት ቤት ሥራዎችና ፕሮግራሞች የማይካፈሉበትን ምክንያት ልናስረዳችሁ እንፈልጋለን። ወዲያውም አመለካከታችንን በሌሎች ላይ ለመጫን ወይም ግድ ተቀበሉን የማለት ፍላጎት እንደሌለን ግልጽ ለማድረግ እንፈልጋለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ