የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • je ገጽ 29
  • ለጽድቅ ሲባል መሰደድ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለጽድቅ ሲባል መሰደድ
  • እንደ አንድ አካል ሆነው በዓለም ዙሪያ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት የይሖዋ ምሥክሮች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ስደት ቢደርስባቸውም ደስተኞች ናቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • ለጽድቅ ሲባል መሰደድ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • አምላክና ቄሣር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • የምትታዘዘው አምላክን ነው ወይስ ሰውን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
ለተጨማሪ መረጃ
እንደ አንድ አካል ሆነው በዓለም ዙሪያ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት የይሖዋ ምሥክሮች
je ገጽ 29

ለጽድቅ ሲባል መሰደድ

ከጓደኞችህ ወይም ከዘመዶችህ የይሖዋ ምሥክሮች በሕግ ረገድ ችግር እንደሚያጋጥማቸው፣ ወይም በአንዳንድ መንግሥታት እንደታገዱ፣ ወይም መጥፎ ሰዎች እንደሆኑ ሰምተህ ይሆናል። እንዲህ ያለ መጥፎ ወሬ የሚወራባቸው ለምንድን ነው?

ይህ ሁሉ የሚደርስባቸው ምሥክሮቹ ሕግ የማያከብሩ ስለሆኑ ሳይሆን የኢየሱስን ፈለግ ስለሚከተሉ ነው። ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ሰዎች እንደሚነቅፏቸው፣ እንደሚያሳድዷቸውና ማንኛውንም ክፉ ነገር በውሸት እንደሚናገሩባቸው ነግሯቸዋል። ይህም የሆነበት ምክንያት የአምላክ ዋነኛ ተቃዋሚ የሆነው ሰይጣን የዚህ ዓለም አምላክ ስለሆነና ሰዎች አምላክን እንዳያገለግሉ ለማድረግ ስለሚፈልግ ነው።—ማቴዎስ 5:10–12፤ 10:16–22, 34–39፤ 24:9, 10፤ ዮሐንስ 15:17 እስከ 16:3፤ 2 ጢሞቴዎስ 3:12፤ 1 ጴጥሮስ 5:8፤ ራእይ 12:17

ሐዋርያት ታስረው ወደ ፍርድ ቤት ይቀርቡ የነበረው ወንጀለኞች ወይም የዓመፅ ሰዎች ወይም በመንግሥት ላይ አድማ የሚያነሣሱ ስለነበሩ አይደለም። የምሥራቹን ይሰብኩ ስለነበረ ብቻ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ ጉዳዩ በበላይ ፍርድ ቤቶች እንዲታይለት ይግባኝ ያለው ክርስቲያኖች የምሥራቹን ለመስበክ ያላቸውን መብት በሕግ ለመከላከልና ለማስከበር ነበር።—ሥራ 4:​18–20፤ 5:28–32፤ ፊልጵስዩስ 1:7

ዛሬም ቢሆን የይሖዋ ምሥክሮች የሚፈለግባቸውን ግብር የሚከፍሉና ባለ ሥልጣኖችንና ሕግን አክባሪ የሆኑ ክርስቲያኖች ናቸው። የቄሣርን ለቄሣር የአምላክንም ለአምላክ ይሰጣሉ። ከማንኛውም መንግሥት ጋር የሚጋጩት ያ መንግሥት የስብከት ሥራቸውን ሲከለክል ወይም በብሔራት መካከል በሚነሡ ግጭቶች ገለልተኞች ስለሚሆኑ ነው። በዚህ ረገድ የይሖዋ ምሥክሮች “ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል” በማለት የተናገሩትን የሐዋርያት አቋም ይይዛሉ።—ሥራ 5:29፤ ማርቆስ 12:17፤ ዮሐንስ 18:36፤ ቲቶ 3:1, 2

የይሖዋ ምሥክሮች ስደት እንዲደርስባቸው አይፈልጉም። በጸጥታና በእርጋታ ቢኖሩ ይመርጣሉ። ይሁን እንጂ የአምላክን ሕግና የኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌ በመከተላቸው ምክንያት ስደት ሲደርስባቸው በመጽናት የሚደርስባቸውን ስደት በደስታ ይቋቋማሉ።—ማቴዎስ 5:10–12፤ ሥራ 5:40, 41፤ 1 ቆሮንቶስ 4:12፤ 1 ጢሞቴዎስ 2:2፤ 1 ጴጥሮስ 3:14, 15፤ 4:12–16

● የይሖዋ አገልጋዮች የሚሰደቡትና የሚሰደዱት ለምንድን ነው?

● አንዳንድ ጊዜ የይሖዋ ምሥክሮች እንደ ሐዋርያት ከመንግሥት ባለ ሥልጣኖች ጋር የሚጋጩት ለምንድን ነው?

● የይሖዋ አገልጋዮች ስደትን እንዴት ይመለከታሉ?

[በገጽ 29 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]

ኢየሱስ በጲላጦስ ፊት ታስሮ የቀረበውና ሐዋርያው ጳውሎስም የታሠረው የአምላክን መንግሥት ስለሰበኩ ነበር

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ