የጀርባ ሽፋን
ያለንበት ዓለም በችግር የተሞላ ነው። ብዙ ትዳሮች ይፈርሳሉ። በቤተሰብ ውስጥ የሚፈጸም ዓመፅ እየተስፋፋ መጥቷል። በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ይሰቃያሉ። ወንጀል በጣም ከመብዛቱ የተነሣ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ መጥቷል። ሰላምና ደህንነት ማስፈን የሕልም እንጀራ ሆኗል። የዓለም ሁኔታ እንዲህ ዓይነት መልክ የያዘው ለምንድን ነው? መፍትሔ ይኖር ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ ብቻ ሳይሆን ለዕለታዊ ኑሯችን የሚጠቅም መመሪያም ይዞልናል። ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ለማወቅ መጓጓት አይገባንምን?
አንዳንድ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ እንዲሁ ተረት፣ አፈ ታሪክና ሰብዓዊ ጥበብ የሞላበት መጽሐፍ ነው የሚል እምነት አላቸው። ይሁንና ሌሎች ደግሞ በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ የአምላክ ቃል ነው ብለው ያምናሉ። ትክክለኛው አመለካከት የትኛው ነው? መጽሐፍ ቅዱስ —የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው? የተባለው ይህ መጽሐፍ የዚህን ጥያቄ መልስ እንድታገኝ ይረዳሃል። ማስረጃዎቹን ራስህ እንድትመረምር እናበረታታሃለን። እንዲህ ማድረግህ ሕይወትህን ለዘላለምም የሚለውጥ ሊሆን ይችላል።