እድገት ማድረግህን ቀጥል
በእያንዳንዱ ምክር መስጫ ነጥብ ሠርተህበታል? የቀረቡትን መልመጃዎች በሙሉ ሠርተህባቸዋል? በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤትም ሆነ በሌሎች ስብሰባዎች ላይ ንግግር ስታቀርብ እንዲሁም በአገልግሎት ስትካፈል የተማርከውን እያንዳንዱን ነጥብ እየሠራህበት ነው?
በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና መጠቀምህን ቀጥል። ለረጅም ዓመት በተደጋጋሚ ንግግር ስታቀርብ የነበረ ቢሆንም እንኳ ልታሻሽል የምትችልባቸው ዘርፎች ይኖራሉ።