ክፍል 4
ትምህርት ቤትና እኩዮችህ
በአንዳንድ የትምህርት ዓይነቶች ማለፊያ ውጤት እንኳ ማምጣት ያስቸግርሃል?
□ አዎ
□ አይ
በትምህርት ቤት ልጆች አስፈራርተውህ አሊያም ፆታዊ ትንኮሳ አጋጥሞህ ያውቃል?
□ አዎ
□ አይ
እንደ እኩዮችህ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ለመፈጸም የሚቃጣህ ጊዜ አለ?
□ አዎ
□ አይ
‘በትምህርት ቤት የሚያጋጥሙኝን ችግሮች አሸንፌ ትምህርቴን ማጠናቀቅ ከቻልኩ ከዚያ በኋላ ማንኛውንም ችግር መወጣት እችላለሁ!’ ብለህ ታስብ ይሆናል። ይህ አባባል በተወሰነ መጠን እውነትነት አለው። ደግሞም ትምህርት ቤት አእምሯዊ፣ ስሜታዊና መንፈሳዊ ጥንካሬህ የሚፈተንበት ቦታ ነው። የአምላክን መመሪያዎች መከተል የማይፈልጉ በትምህርት ቤት ያሉ አንዳንድ እኩዮችህ በሚያሳድሩብህ መጥፎ ተጽዕኖ ሳትሸነፍ ጥሩ ትምህርት መቅሰም የምትችለው እንዴት ነው? ከ13 እስከ 17 ያሉት ምዕራፎች በዚህ ረገድ የሚያስፈልግህን ብቃት እንድታዳብር ይረዱሃል።
[በገጽ 112 እና 113 ላይ የሚገኝ ባለ ሙሉ ገጽ ሥዕል]