መዝሙር 54
ጠንካራ እምነት ሊኖረን ይገባል
በወረቀት የሚታተመው
1. ይሖዋ ብዙ ጊዜ ተናግሯል፤
በጥንት ነብያቱ በኩል።
ዛሬም ‘ንስሐ ግቡ’ ይለናል፤
በገዛ ልጁ በኩል።
(አዝማች)
ጽኑ ነው ወይ እምነታችን?
ሊያበቃን ’ሚችል ለመዳን?
ይታያል ወይ በሥራችን?
ይህ ዓይነት እምነት ነው የሚያድነን።
2. ክርስቶስን እንታዘዛለን፤
እውነትን እናስፋፋለን።
የመናገር ነፃነቱ አለን፤
አንሸሽግም መል’ክቱን።
(አዝማች)
ጽኑ ነው ወይ እምነታችን?
ሊያበቃን ’ሚችል ለመዳን?
ይታያል ወይ በሥራችን?
ይህ ዓይነት እምነት ነው የሚያድነን።
3. የማይናወጥ ነው እምነታችን፤
ፍርሃትም አያሸንፈን።
ቢነሱብንም ጠላቶቻችን፣
ይታየን መዳናችን።
(አዝማች)
ጽኑ ነው ወይ እምነታችን?
ሊያበቃን ’ሚችል ለመዳን?
ይታያል ወይ በሥራችን?
ይህ ዓይነት እምነት ነው የሚያድነን።