መዝሙር 93
“ብርሃናችሁ ይብራ”
በወረቀት የሚታተመው
1. ብርሃን ’ንድናበራ ጌታ አዞናል፤
ምንም ሳናዳላ ልክ እንደ ፀሐይ።
ያምላክ ቃል ጥበብን ፈንጥቆልናል፤
ብርሃኑን እናንጸባርቅ በመልካም ጠባይ።
2. ምሥራቹ በሰው ልብ ውስጥ ያበራል፤
መጽናናትንና ተስፋን ይሰጣል።
ቃሉ ይመራናል ብርሃናችን ነው፤
ለዛ ባለው አንደበት ድምቀት እንስጠው።
3. መልካሙ ሥራችን ብርሃን ያበራል፤
ለትምህርታችንም ድምቀት ይሰጣል።
እንቀጥል ብርሃን ማብራታችንን፤
ይህ ነው በይሖዋ ዘንድ የሚያስወድደን።
(በተጨማሪም መዝ. 119:130ን፣ ማቴ. 5:14, 15, 45ን እና ቆላ. 4:6ን ተመልከት።)