የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • bm ክፍል 4 ገጽ 7
  • አምላክ ከአብርሃም ጋር ቃል ኪዳን ገባ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ ከአብርሃም ጋር ቃል ኪዳን ገባ
  • መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አብርሃም ማን ነበር?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ይሖዋ “ወዳጄ” በማለት ጠርቶታል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • አብርሃም እና ሣራ—እምነታቸውን መኮረጅ ትችላለህ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • አብርሃምና ሣራ አምላክን ታዘዋል
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
ለተጨማሪ መረጃ
መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
bm ክፍል 4 ገጽ 7
አብርሃም ከዋክብትን ሲመለከት

ክፍል 4

አምላክ ከአብርሃም ጋር ቃል ኪዳን ገባ

አብርሃም አምላክን በእምነት በመታዘዙ ይሖዋ እንደሚባርከውና ዘሩንም እንደሚያበዛለት ቃል ገባለት

በኖኅ ዘመን ከመጣው የጥፋት ውኃ በኋላ ወደ 350 የሚጠጉ ዓመታት አለፉ። የቤተሰብ ራስ የነበረው አብርሃም፣ ዑር (በዛሬዋ ኢራቅ ውስጥ ትገኛለች) በምትባል የበለጸገች ከተማ ውስጥ ይኖር ነበር። አብርሃም ታላቅ እምነት ያለው ሰው ነበር። ይሁን እንጂ እምነቱን የሚፈትን ነገር አጋጠመው።

ይሖዋ፣ አብርሃም የተወለደበትን አገር ትቶ ከነዓን ወደሚባል ባዕድ አገር እንዲሄድ ነገረው። አብርሃምም ያለማወላወል ታዘዘ። ሚስቱን ሣራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን ጨምሮ ቤተሰቡን በመያዝ ረጅም ጉዞ ካደረገ በኋላ በከነዓን ምድር በድንኳን ውስጥ መኖር ጀመረ። ይሖዋ አብርሃምን ታላቅ ሕዝብ እንደሚያደርገው፣ የምድር ሕዝቦች በሙሉ በእሱ አማካኝነት እንደሚባረኩ እንዲሁም ዘሩ የከነዓንን ምድር እንደሚወርስ በመግለጽ ከእሱ ጋር ቃል ኪዳን ገባ።

አብርሃምና ሎጥ ብዙ የበጎችና የከብቶች መንጋ ያላቸው ባለጸጎች ሆኑ። ራስ ወዳድ ያልሆነው አብርሃም፣ የሚፈልገውን አካባቢ እንዲመርጥ ለሎጥ ፈቀደለት። ሎጥ በዮርዳኖስ ወንዝ አካባቢ ያለውን ለምለም ቦታ በመምረጥ በሰዶም ከተማ አቅራቢያ ሰፈረ። የሰዶም ሰዎች ግን መጥፎ ሥነ ምግባር ያላቸውና በይሖዋ ፊት እጅግ ኃጢአተኞች ነበሩ።

ይሖዋ አምላክ፣ የአብርሃም ዘሮች እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደሚበዙ ለአብርሃም አረጋገጠለት። አብርሃምም ይሖዋ በሰጠው በዚህ ተስፋ አመነ። ሆኖም የሚወዳት ሚስቱ ሣራ መካን ነበረች። አብርሃም 99 ዓመት ሲሆነው ሣራ ደግሞ 90 ዓመት ሊሞላት ሲቃረብ አምላክ ወንድ ልጅ እንደሚወልዱ ለአብርሃም ነገረው። አምላክ እንደተናገረውም ሣራ ይስሐቅን ወለደች። አብርሃም ሌሎች ልጆች የነበሩት ቢሆንም በኤደን ተስፋ የተሰጠበት አዳኝ የሚመጣው በይስሐቅ በኩል ነበር።

በዚህ ጊዜ ሎጥና ቤተሰቡ የሚኖሩት በሰዶም ነበር፤ ያም ቢሆን ጻድቁ ሎጥ በከተማዋ የነበሩትን መጥፎ ሥነ ምግባር ያላቸው ሰዎች አልተከተለም። ይሖዋ ሰዶምን ለማጥፋት በወሰነ ጊዜ ስለሚመጣው ጥፋት ሎጥን እንዲያስጠነቅቁት መላእክትን ላከ። መላእክቱ፣ ሎጥንና ቤተሰቡን ከሰዶም እንዲሸሹና ወደኋላቸው እንዳይመለከቱ አሳስበዋቸው ነበር። ከዚያም አምላክ በሰዶምና በአቅራቢያዋ በምትገኘው ገሞራ የተባለች ክፉዎች የሞሉባት ከተማ ላይ እሳትና ዲን በማዝነብ ነዋሪዎቹን በሙሉ አጠፋቸው። ሎጥና ሁለቱ ሴት ልጆቹ ከጥፋቱ ዳኑ። የሎጥ ሚስት ግን ትታው ስለመጣችው ነገር በማሰብ ሳይሆን አይቀርም ወደኋላ ዞራ ተመለከተች። ባለመታዘዟም ሕይወቷን አጣች።

—በዘፍጥረት 11:10 እስከ 19:38 ላይ የተመሠረተ።

  • አብርሃም ወደ ከነዓን የሄደው ለምን ነበር?

  • ይሖዋ ከአብርሃም ጋር ምን ቃል ኪዳን ገባ?

  • ይሖዋ ሰዶምንና ገሞራን ያጠፋቸው ለምን ነበር?

የቃል ኪዳን አምላክ

በጥንት ዘመን፣ ቃል ኪዳን ሲባል ውልን ወይም ስምምነትን ያመለክት ነበር። ይሖዋ በተከታታይ በገባቸው ቃል ኪዳኖች አማካኝነት፣ በኤደን ተስፋ ከተሰጠበት አዳኝ ጋር በተያያዘ ያለው ዓላማ እንዴት እንደሚፈጸም ደረጃ በደረጃ ገልጿል። አምላክ ከአብርሃም ጋር የገባው ቃል ኪዳን፣ ተስፋ የተሰጠበት አዳኝ የሚመጣው በአብርሃም የዘር ሐረግ በኩል እንደሆነ ያመለክት ነበር። ይሖዋ ከዚያ በኋላ የገባቸው ሌሎች ቃል ኪዳኖችም የዚህን አዳኝ ማንነት በተመለከተ ተጨማሪ የእውቀት ብርሃን የሚፈነጥቁ ነበሩ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ