የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • bm ክፍል 8 ገጽ 11
  • የእስራኤል ሕዝብ ወደ ከነዓን ገባ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የእስራኤል ሕዝብ ወደ ከነዓን ገባ
  • መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የኢያሱ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • ረዓብ “በሥራ ጻድቅ ተብላ” ተጠርታለች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ረዓብ ሰላዮቹን ደበቀች
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ኢያሱ ካሳለፈው ተሞክሮ ያገኘው ጥቅም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
ለተጨማሪ መረጃ
መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
bm ክፍል 8 ገጽ 11
ካህናቱ ቀንደ መለከቱን ሲነፉ ኢያሱ የጦርነት ጩኸት ሲያሰማ

ክፍል 8

የእስራኤል ሕዝብ ወደ ከነዓን ገባ

እስራኤላውያን በኢያሱ እየተመሩ የከነዓንን ምድር ድል አድርገው ያዙ። መሳፍንት ሕዝቡን ከጭቆና ነፃ እንዲያወጡ ይሖዋ ኃይል ሰጣቸው

እስራኤላውያን ወደ ከነዓን ምድር ከመግባታቸው ከበርካታ ዘመናት በፊት ይሖዋ ይህንን ምድር ለአብርሃም ዘሮች እንደሚሰጥ ቃል ገብቶ ነበር። አሁን እስራኤላውያን ኢያሱ እየመራቸው የተስፋይቱን ምድር ሊወርሱ ተዘጋጅተዋል።

አምላክ፣ ከነዓናውያን መጥፋት እንደሚገባቸው ፈርዶባቸው ነበር። እነዚህ ሕዝቦች እጅግ ወራዳ በሆኑ የብልግና ድርጊቶችና ገደብ በሌለው ደም መፋሰስ ምድሪቱን በክለዋት ነበር። በዚህም ምክንያት እስራኤላውያን ድል የሚያደርጓቸው የከነዓናውያን ከተሞች ሙሉ በሙሉ መጥፋት ነበረባቸው።

እስራኤላውያን ወደ ከነዓን ምድር ከመግባታቸው በፊት ግን ኢያሱ ሁለት ሰላዮችን ላከ፤ ሰላዮቹም ወደ ኢያሪኮ ከተማ ገብተው ረዓብ የምትባል ሴት ቤት አደሩ። ረዓብ፣ ሰላዮቹ እስራኤላውያን መሆናቸውን ብታውቅም በቤቷ ተቀብላ ሸሸገቻቸው። ረዓብ፣ ይሖዋ ሕዝቡ እንዴት እንዳዳናቸው ሰምታ ስለነበር በእስራኤላውያን አምላክ ላይ እምነት ነበራት። ሰላዮቹ እሷንና ቤተሰቧን እንደሚያድኑ እንዲምሉላት አደረገች።

እስራኤላውያን ወደ ከነዓን ምድር ገብተው በኢያሪኮ ላይ ሲዘምቱ ይሖዋ የኢያሪኮ ቅጥር በተአምራዊ መንገድ እንዲወድቅ አደረገ። ከዚያም የኢያሱ ሠራዊት ወደ ከተማይቱ ሰተት ብሎ በመግባት ኢያሪኮን አጠፋት፤ ረዓብንና ቤተሰቧን ግን አዳኗቸው። ከዚያም ኢያሱ በስድስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የተስፋይቱን ምድር አብዛኛውን ክፍል ተቆጣጠረ። ከዚያ በኋላ ምድሪቱ ለእስራኤል ነገዶች ተከፋፈለች።

የከነዓን ምድር ካርታ[በገጽ 11 ላይ የሚገኝ ግራፍ ካርታ]

ኢያሱ ይሖዋን በማገልገል ባሳለፋቸው ረጅም ዓመታት መገባደጃ ላይ ሕዝቡን አንድ ላይ ሰበሰባቸው። ከዚያም ይሖዋ ለቀድሞ አባቶቻቸው ያደረገውን ነገር ካስታወሳቸው በኋላ ይሖዋን እንዲያገለግሉ አበረታታቸው። ይሁን እንጂ ኢያሱና ከእሱ ጋር ሆነው ይሖዋን ያገለገሉት በዕድሜ የገፉ ሰዎች ሁሉ ከሞቱ በኋላ እስራኤላውያን ይሖዋን ትተው የሐሰት አማልክትን ማምለክ ጀመሩ። ሕዝቡ ለ300 ዓመታት ያህል፣ አንዳንድ ጊዜ የይሖዋን ሕግ ይታዘዙ በሌሎች ጊዜያት ግን ሕግጋቱን በመጣስ ሌሎች አማልክትን ያመልኩ ነበር። በዚያ ወቅት ይሖዋ፣ እንደ ፍልስጤማውያን ያሉት የእስራኤል ጠላቶች ሕዝቡን እንዲጨቁኗቸው ፈቀደ። ይሁን እንጂ እስራኤላውያን ይሖዋ እንዲረዳቸው ወደ እሱ በሚጮኹበት ጊዜ መሳፍንትን ያስነሳላቸው ነበር፤ ሕዝቡን ከጭቆና እንዲያድኗቸው በጠቅላላው 12 መሳፍንትን አስነስቶላቸዋል።

በመሳፍንት መጽሐፍ ውስጥ የሚገኘው ስለ መሳፍንት ዘመን የሚገልጸው ዘገባ በጎቶንያል ታሪክ ጀምሮ በሳምሶን ያበቃል፤ ሳምሶን በምድር ላይ ከኖሩት ሰዎች ሁሉ በአካላዊ ጥንካሬው ተወዳዳሪ የለውም። የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በሆነው በመሳፍንት መጽሐፍ ውስጥ በሰፈሩት ስሜት ቀስቃሽ ዘገባዎች ላይ ተደጋግሞ የተገለጸው መሠረታዊ እውነት የሚከተለው ነው፦ ይሖዋን መታዘዝ በረከትን የሚያስገኝ ሲሆን አለመታዘዝ ደግሞ ከባድ መዘዝ ያስከትላል።

—በኢያሱና በመሳፍንት መጻሕፍት እንዲሁም በዘሌዋውያን 18:24, 25 ላይ የተመሠረተ።

  • ይሖዋ ረዓብንና ቤተሰቧን ያዳናቸው ለምን ነበር?

  • እስራኤላውያን ኢያሱ ከሞተ በኋላ ምን አደረጉ?

  • በመሳፍንት መጽሐፍ ውስጥ የተገለጸው መሠረታዊ እውነት ምንድን ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ