የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • bm ክፍል 12 ገጽ 15
  • ለሕይወት መመሪያ የሚሆን አምላካዊ ጥበብ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለሕይወት መመሪያ የሚሆን አምላካዊ ጥበብ
  • መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ምሳሌ 3:5, 6—“በገዛ ራስህ ማስተዋል አትመካ”
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው
  • ጥበብን አግኝ ተግሣጽንም ተቀበል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ምሳሌ 22:6—“ልጅን ሊሄድበት በሚገባው መንገድ አሠልጥነው”
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው
  • ሰለሞን ጠቢብ ንጉሥ ነበር
    መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
bm ክፍል 12 ገጽ 15
በጥንት ዘመን የሚኖሩ ሰዎች እህል ሲሰበስቡ

ክፍል 12

ለሕይወት መመሪያ የሚሆን አምላካዊ ጥበብ

የምሳሌ መጽሐፍ ለዕለት ተዕለት ሕይወታችን መመሪያ የሚሆን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፈ ምክር የተሰባሰበበት ጥራዝ ነው፤ የዚህን መጽሐፍ አብዛኛውን ክፍል የጻፈው ሰለሞን ነው

ይሖዋ ጥበበኛ ገዥ ነው? ለዚህ ጥያቄ በማያሻማ መልኩ መልስ ማግኘት የሚቻልበት አንዱ መንገድ እሱ የሚሰጠውን ምክር መመርመር ነው። ይሖዋ የሚሰጠው ምክር ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ነው? ምክሩን በሥራ ላይ ማዋል ይበልጥ ትርጉም ያለውና የተሻለ ሕይወት ለመምራት ይረዳል? ጠቢቡ ንጉሥ ሰለሞን በመቶዎች የሚቆጠሩ ምሳሌዎችን ጽፏል። እነዚህ ምሳሌዎች ሁሉንም የሕይወት ዘርፍ የሚዳስሱ ናቸው ለማለት ይቻላል። እስቲ አንዳንድ ምሳሌዎችን እንመልከት።

በአምላክ መተማመን። ከይሖዋ ጋር ጥሩ ዝምድና ለመመሥረት በእሱ መተማመን ወሳኝ ነገር ነው። ሰለሞን እንደሚከተለው በማለት ጽፏል፦ “በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፤ በራስህ ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን ዕወቅ፤ እርሱም ጐዳናህን ቀና ያደርገዋል።” (ምሳሌ 3:5, 6) የይሖዋን አመራር በመሻትና እሱን በመታዘዝ በአምላክ መተማመናችን ሕይወታችን ይበልጥ ትርጉም ያለው እንዲሆን ያደርጋል። አንድ ሰው እንዲህ ዓይነቱን አካሄድ መከተሉ የአምላክን ልብ ደስ የሚያሰኝ ከመሆኑም ሌላ የይሖዋ ጠላት የሆነው ሰይጣን ላነሳቸው አከራካሪ ጉዳዮች መልስ ለመስጠት ያስችላል።—ምሳሌ 27:11

ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት በጥበብ መመላለስ። አምላክ ለባሎች፣ ለሚስቶችና ለልጆች የሰጠው ምክር ከምንጊዜውም ይበልጥ ዛሬ ወቅታዊ ነው። አምላክ “በልጅነት ሚስትህም ደስ ይበልህ” በማለት ባል ለሚስቱ ታማኝ እንዲሆን ይመክራል። (ምሳሌ 5:18-20) ያገቡ ሴቶች ደግሞ የባሏንና የልጆቿን አድናቆት ስላተረፈች አንዲት ባለሞያ ሚስት የሚገልጽ ግሩም ሐሳብ በምሳሌ መጽሐፍ ውስጥ ያገኛሉ። (ምሳሌ ምዕራፍ 31) ልጆችም ወላጆቻቸውን እንዲታዘዙ የሚያሳስብ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል። (ምሳሌ 6:20) በተጨማሪም አንድ ሰው ራሱን ማግለሉ ራስ ወዳድ ወደ መሆን ስለሚመራው ከሌሎች ጋር ወዳጅነት መመሥረት አስፈላጊ መሆኑን የምሳሌ መጽሐፍ ይጠቁማል። (ምሳሌ 18:1) ጓደኞች በጎም ሆነ መጥፎ ተጽዕኖ ሊያሳድሩብን ስለሚችሉ ወዳጆቻችንን በጥበብ መምረጥ ያስፈልገናል።—ምሳሌ 13:20፤ 17:17

ጥበበኛ በመሆን ራሳችንን መንከባከብ። የምሳሌ መጽሐፍ የአልኮል መጠጥን ከመጠን በላይ ከመጠጣት እንድንቆጠብ፣ ለጤናችን የሚበጁ ባሕርያትን እንድናዳብርና ጎጂ የሆኑትን እንድናስወግድ እንዲሁም ታታሪ ሠራተኛ እንድንሆን የሚያበረታቱ በዋጋ የማይተመኑ ጠቃሚ ምክሮችን ይዟል። (ምሳሌ 6:6፤ 14:30፤ 20:1) ከአምላክ መመሪያዎች ጋር በማይስማሙ ሰብዓዊ ምክሮች መታመን ወደ ጥፋት እንደሚመራ ያስጠነቅቃል። (ምሳሌ 14:12) “የሕይወት ምንጭ” ልብ መሆኑን በማሳሰብ ውስጣዊ ማንነታችንን ማለትም ልባችንን ሊበክሉ ከሚችሉ ተጽዕኖዎች እንድንጠብቅ ይመክረናል።—ምሳሌ 4:23

በመላው ዓለም የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እንደነዚህ ባሉት ምክሮች መመራት የተሻለ ሕይወት እንደሚያስገኝ ተገንዝበዋል። በዚህም ምክንያት ይሖዋን እንደ ገዥያቸው አድርገው ለመቀበል በቂ ምክንያት እንዳላቸው ይሰማቸዋል።

—በምሳሌ መጽሐፍ ላይ የተመሠረተ።

  • የምሳሌ መጽሐፍን በማጥናት ምን ልንማር እንችላለን?

  • የምሳሌ መጽሐፍ በአምላክ ስለ መተማመን እንዲሁም ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት በጥበብ ስለ መመላለስና ራሳችንን ስለ መንከባከብ ምን መመሪያ ይሰጣል?

መክብብ

ሕይወት ትርጉም ያለው እንዲሆን ማድረግ እንዲሁም እርካታ ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው? ሰለሞን የዚህን ጥያቄ መልስ ለማግኘት የሚያስችል ጥሩ አጋጣሚ ነበረው። እጅግ ከፍተኛ ሀብት፣ ጥበብና ሥልጣን ስለነበረው እነዚህ ነገሮች እውነተኛ ደስታ ያስገኙለት እንደሆነና እንዳልሆነ ለመፈተን ችሎ ነበር። ቁሳዊ ነገሮችን በማሳደድ ተድላ ለማግኘት ሞክሯል፣ ብዙ ውብ ሴቶችን አግብቷል፤ እንዲሁም አሉ በተባሉ መዝናኛዎች ሁሉ ተዝናንቷል። ታላላቅ የግንባታ ሥራዎችን አካሂዷል። ምሑራን ያዘጋጇቸውን መጻሕፍት መርምሯል። ታዲያ ምን አግኝቶ ይሆን? ሰለሞን “ሁሉም ነገር ከንቱ ነው!” ብሏል። ይሁን እንጂ በመግቢያው ላይ ላነሳነው ጥያቄ መልስ ለማግኘት ሲጥር ከቆየ በኋላ የሚከተለውን እውነታ ተገንዝቧል፦ “እነሆ፤ ሁሉ ነገር ከተሰማ ዘንድ፣ የነገሩ ሁሉ ድምዳሜ ይህ ነው፤ እግዚአብሔርን ፍራ፤ ትእዛዛቱንም ጠብቅ፤ ይህ የሰው ሁለንተናዊ ተግባሩ ነውና።”—መክብብ 12:8, 13

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ