የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • bm ክፍል 19 ገጽ 22
  • ኢየሱስ መላውን ዓለም የሚነካ ትንቢት ተናገረ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ መላውን ዓለም የሚነካ ትንቢት ተናገረ
  • መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሐዋርያቱ ምልክት እንዲሰጣቸው ኢየሱስን ጠየቁት
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • አርማጌዶን እንደቀረበ ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • “መጨረሻው” ስለሚለው ቃል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • የክርስቶስ መገኘት ለአንተ ምን ትርጉም አለው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
ለተጨማሪ መረጃ
መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
bm ክፍል 19 ገጽ 22
ኢየሱስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሆኖ ከአንዳንድ ሐዋርያቱ ጋር ሲነጋገር

ክፍል 19

ኢየሱስ መላውን ዓለም የሚነካ ትንቢት ተናገረ

ኢየሱስ፣ በንጉሣዊ ሥልጣኑ መገኘቱንና የዚህ ሥርዓት መደምደሚያ መቅረቡን የሚጠቁሙ ምልክቶችን ተናገረ

ኢየሱስ፣ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ኢየሩሳሌምንና ቤተ መቅደሷን ቁልቁል ማየት በሚቻልበት ቦታ ተቀምጦ ሳለ ከሐዋርያቱ መካከል አራቱ ለብቻቸው ወደ እሱ ቀርበው ቀደም ሲል ስለተናገረው ነገር ጠየቁት። ኢየሱስ በኢየሩሳሌም የሚገኘው ቤተ መቅደስ እንደሚጠፋ ተናግሮ ነበር። ከዚያ ቀደም ብሎ በሌላ ጊዜ ደግሞ ‘ስለዚህ ሥርዓት መደምደሚያ’ ገልጾ ነበር። (ማቴዎስ 13:40, 49) በዚህ ወቅት ሐዋርያቱ “የመገኘትህና የዚህ ሥርዓት መደምደሚያ ምልክትስ ምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት።—ማቴዎስ 24:3

ኢየሱስ ለሐዋርያቱ በሰጠው መልስ ላይ ኢየሩሳሌም ከመጥፋቷ በፊት ስለሚፈጸሙ ነገሮች ገልጾ ነበር። ይሁን እንጂ የተናገረው ነገር ኢየሩሳሌም ከጠፋች በኋላ ወደፊት የሚፈጸሙትን ክንውኖችም ያመለክታል። ኢየሱስ የተናገረው ትንቢት ከጊዜ በኋላ በመላው ዓለም ላይ ታላቅ ፍጻሜ ይኖረዋል። ኢየሱስ ወደፊት በዓለም ላይ ስለሚፈጸሙ ሁኔታዎችና ክስተቶች ትንቢት ተናግሯል፤ እነዚህ ሁሉ ክንውኖች በአንድ ላይ ተጣምረው መፈጸማቸው ኢየሱስ በሰማይ ንጉሥ ሆኖ የሚገኝበት ጊዜ መጀመሩን በምድር ላይ ለሚኖሩ ሰዎች ምልክት ይሆናቸዋል። በሌላ አነጋገር ይህ ምልክት፣ ይሖዋ አምላክ ኢየሱስን ከረጅም ጊዜ በፊት ተስፋ የተሰጠበት መሲሐዊ መንግሥት ንጉሥ እንዳደረገው ይጠቁማል። ይህ ምልክት የአምላክ መንግሥት ክፋትን የሚያስወግድበትና ለሰው ልጆች እውነተኛ ሰላም የሚያመጣበት ጊዜ መቅረቡንም ያሳያል። በመሆኑም ኢየሱስ የተነበያቸው ነገሮች፣ አሁን ያለውን ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ እንዲሁም ማኅበራዊ ሥርዓት ያቀፈው አሮጌው ሥርዓት በመጨረሻው ቀን ላይ እንደሚገኝና አዲስ ሥርዓት የሚጀምርበት ጊዜ እንደቀረበ ያመለክታሉ።

ኢየሱስ በሰማይ ንጉሥ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ በምድር ላይ የሚፈጸሙትን ነገሮች ሲገልጽ ዓለም አቀፍ ጦርነቶች፣ የምግብ እጥረትና ታላላቅ የምድር መናወጦች እንደሚኖሩ እንዲሁም በብዙ ቦታዎች በሽታ እንደሚስፋፋ ተናግሯል። ሕገ ወጥነት ይስፋፋል። የኢየሱስ እውነተኛ ደቀ መዛሙርት የአምላክን መንግሥት ምሥራች በመላው ምድር ላይ ይሰብካሉ። እነዚህ ሁሉ ነገሮች እስከዛሬ ድረስ ሆኖ በማያውቅ “ታላቅ መከራ” ይደመደማሉ።—ማቴዎስ 24:21

ታዲያ የኢየሱስ ተከታዮች ይህ መከራ መቅረቡን የሚያውቁት እንዴት ነው? ኢየሱስ “የበለስን ዛፍ እንደ ምሳሌ በመውሰድ . . . ተማሩ” ብሏል። (ማቴዎስ 24:32) የበለስ ቅጠሎች በዛፉ ቅርንጫፎች ላይ ማቆጥቆጣቸው በጋ መቅረቡን የሚያሳይ ምልክት ነው። በተመሳሳይም ኢየሱስ በትንቢት የተናገራቸው ነገሮች በሙሉ በአንድ ወቅት ላይ መፈጸማቸው መጨረሻው መቅረቡን የሚያሳይ ግልጽ ምልክት ይሆናል። እርግጥ ነው፣ ታላቁ መከራ የሚጀምርበትን ትክክለኛ ቀንና ሰዓት ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም። በመሆኑም ኢየሱስ “የተወሰነው ጊዜ መቼ እንደሆነ ስለማታውቁ . . . ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ” በማለት ደቀ መዛሙርቱን መክሯቸዋል።—ማርቆስ 13:33

—በማቴዎስ ምዕራፍ 24 እና 25፤ በማርቆስ ምዕራፍ 13 እንዲሁም በሉቃስ ምዕራፍ 21 ላይ የተመሠረተ።

  • የኢየሱስ ሐዋርያት ስለ የትኛው ጉዳይ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ፈልገው ነበር?

  • ኢየሱስ የሰጠው ምልክት ምን ትርጉም አለው? የዚህ ምልክት አንዳንድ ገጽታዎች ምንድን ናቸው?

  • ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ምን ምክር ሰጥቷቸዋል?

የክርስቶስን መገኘት የሚጠቁመው ምልክት

አምላክ፣ ብልሹ የሆነውን ያለንበትን ሥርዓት የሚያጠፋበት ጊዜ መቅረቡን የሚጠቁም ምልክት እንደሚኖር ኢየሱስ ተንብዮአል። ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ጀምሮ የሰው ዘር፣ ኢየሱስ የተነበየው ነገር ሲፈጸም ተመልክቷል። በመላው ዓለም የሚታዩት ሃይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ክስተቶች ይህ ሥርዓት ወደማይቀረው ፍጻሜው በፍጥነት እንዲገሠግሥ እያደረጉ ነው። የኢየሱስ ተከታዮች ከጥፋት ለመትረፍ ‘ነቅተው መጠበቅ’ እንዲሁ በአምላክ ሉዓላዊነት ላይ በተነሳው ጥያቄ ረገድ ከአምላክ ጎን ለመቆም በቆራጥነት እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ኢየሱስ አስተምሯል።a—ሉቃስ 21:36፤ ማቴዎስ 24:3-14

a ኢየሱስ የተናገረውን ትንቢት በተመለከተ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀ መጽሐፍ ምዕራፍ 9 ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ