የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • bm ክፍል 24 ገጽ 27-28
  • ጳውሎስ ለጉባኤዎች ደብዳቤ ጻፈ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጳውሎስ ለጉባኤዎች ደብዳቤ ጻፈ
  • መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እምነትን፣ ምግባርንና ፍቅርን በተመለከተ የተሰጠ ምክር
    መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
  • ጢሞቴዎስ ‘በእምነት እውነተኛ ልጅ የሆነ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ጳውሎስ በሮም
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ አጠቃላይ ስምምነት
    መጽሐፍ ቅዱስ—የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?
ለተጨማሪ መረጃ
መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
bm ክፍል 24 ገጽ 27-28
ጳውሎስ የቁም እስረኛ እያለ ደብዳቤ ሲያጽፍ

ክፍል 24

ጳውሎስ ለጉባኤዎች ደብዳቤ ጻፈ

ጳውሎስ የክርስቲያን ጉባኤን የሚያበረታቱ ደብዳቤዎች ጻፈ

አዲስ የተቋቋመው የክርስቲያን ጉባኤ የይሖዋን ዓላማ በማስፈጸም ረገድ ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል። ይሁን እንጂ በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበረው የክርስቲያን ጉባኤ ከተቋቋመ ብዙም ሳይቆይ ጥቃት ይሰነዘርበት ጀመር። በወቅቱ የነበሩት ክርስቲያኖች ከጉባኤው ውጪ የሚደርስባቸውን ስደትም ሆነ በጉባኤ ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን ሌሎች ስውር አደጋዎች ተቋቁመው በአምላክ ፊት ንጹሕ አቋማቸውን ጠብቀው መገኘት ይችሉ ይሆን? በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ክርስቲያኖች የሚያስፈልጋቸውን ምክርና ማበረታቻ የያዙ 21 ደብዳቤዎች ይገኛሉ።

ከሮም እስከ ዕብራውያን ያሉትን አሥራ አራት ደብዳቤዎች የጻፈው ሐዋርያው ጳውሎስ ነው። እነዚህ ደብዳቤዎች የተሰየሙት መልእክቱ በተላከለት ግለሰብ ወይም በአንድ ጉባኤ ስም ነው። በጳውሎስ ደብዳቤዎች ውስጥ የተካተቱትን አንዳንድ ርዕሰ ጉዳዮች እስቲ እንመልከት።

ሥነ ምግባርንና አኗኗርን በተመለከተ የተሰጠ ጠንከር ያለ ምክር። ዝሙት፣ ምንዝር እና ሌሎች ከባድ ኃጢአቶችን የሚፈጽሙ ሰዎች ‘የአምላክን መንግሥት አይወርሱም።’ (ገላትያ 5:19-21፤ 1 ቆሮንቶስ 6:9-11) የአምላክ አገልጋዮች ዜግነታቸው ምንም ይሁን ምን አንድነት ሊኖራቸው ይገባል። (ሮም 2:11፤ ኤፌሶን 4:1-6) ክርስቲያኖች እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን የእምነት ባልንጀሮቻቸውን ለመርዳት በደስታ ራሳቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል። (2 ቆሮንቶስ 9:7) ጳውሎስ “ያለማቋረጥ ጸልዩ” ብሏል። በእርግጥም የአምላክ አገልጋዮች ወደ ይሖዋ ሲጸልዩ የልባቸውን አውጥተው እንዲነግሩት ተበረታተዋል። (1 ተሰሎንቄ 5:17፤ 2 ተሰሎንቄ 3:1፤ ፊልጵስዩስ 4:6, 7) አምላክ ጸሎታቸውን እንዲሰማላቸው ደግሞ በእምነት ሊጸልዩ ይገባል።—ዕብራውያን 11:6

የቤተሰብ ሕይወት ስኬታማ እንዲሆን የሚረዳው ምንድን ነው? ባሎች ሚስቶቻቸውን እንደ ገዛ አካላቸው አድርገው ሊወዷቸው ይገባል። ሚስቶች ባሎቻቸውን በጥልቅ ሊያከብሩ ይገባል። ልጆች ለወላጆቻቸው መታዘዛቸው ጌታን ደስ የሚያሰኝ ስለሆነ ይህን ማድረግ አለባቸው። ወላጆች መለኮታዊ መመሪያዎችን በመጠቀም ልጆቻቸውን በፍቅር መምራትና ማሠልጠን ይኖርባቸዋል።—ኤፌሶን 5:22 እስከ 6:4፤ ቆላስይስ 3:18-21

ጳውሎስ ደብዳቤ የላከባቸው ቦታዎች ካርታ

የአምላክን ዓላማ ለመረዳት የሚያስችል ብርሃን ፈነጠቀ። በሙሴ ሕግ ውስጥ የሚገኙት በርካታ መመሪያዎች ክርስቶስ እስከሚመጣ ድረስ እስራኤላውያንን ለመጠበቅና ለመምራት አገልግለዋል። (ገላትያ 3:24) ይሁንና ክርስቲያኖች ይሖዋን ለማምለክ እነዚህን ሕግጋት የግድ መታዘዝ አያስፈልጋቸውም። ጳውሎስ ከአይሁድ እምነት ለመጡት የዕብራውያን ክርስቲያኖች በጻፈው ደብዳቤ ላይ የሕጉን ትርጉም በተመለከተ ብርሃን የፈነጠቀ ከመሆኑም ሌላ የአምላክ ዓላማ በክርስቶስ በኩል የተፈጸመበትን መንገድ በሚገባ አብራርቷል። ጳውሎስ በሕጉ ውስጥ የነበሩት የተለያዩ ዝግጅቶች ትንቢታዊ ጥላነት እንዳላቸው ገልጿል። ለምሳሌ በሕጉ ሥር የሚቀርበው የእንስሳት መሥዋዕት፣ እውነተኛ የኃጢአት ይቅርታ ለሚያስገኘው የኢየሱስ መሥዋዕታዊ ሞት ጥላ ነበር። (ዕብራውያን 10:1-4) ኢየሱስ ከሞተ በኋላ የሕጉ ቃል ኪዳን አስፈላጊ ባለመሆኑ አምላክ ይህንን ቃል ኪዳን ደመሰሰው።—ቆላስይስ 2:13-17፤ ዕብራውያን 8:13

በጥንት ዘመን የነበረ አንድ ጉባኤ አባላት ከጳውሎስ ደብዳቤዎች አንዱ ሲነበብ እያዳመጡ

ተገቢ የሆነ የጉባኤ አደረጃጀትን በተመለከተ የተሰጠ መመሪያ። በጉባኤ ውስጥ ኃላፊነት ለመሸከም ፈቃደኛ የሆኑ ወንድሞች በላቁ የሥነ ምግባር መሥፈርቶች መመራትና መንፈሳዊ ብቃቶችን ማሟላት ይገባቸዋል። (1 ጢሞቴዎስ 3:1-10, 12, 13፤ ቲቶ 1:5-9) የይሖዋ አምላኪዎች እርስ በርስ ለመበረታታት እንዲችሉ ከእምነት ባልንጀሮቻቸው ጋር አዘውትረው መሰብሰብ ይኖርባቸዋል። (ዕብራውያን 10:24, 25) ለአምልኮ የሚደረጉ ስብሰባዎች የሚያንጹና ትምህርት የሚሰጡ መሆን አለባቸው።—1 ቆሮንቶስ 14:26, 31

ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ሁለተኛውን ደብዳቤ የጻፈው ወደ ሮም ከተመለሰ በኋላ ሲሆን በዚያም እስር ቤት ሆኖ ፍርዱን እየተጠባበቀ ነበር። በወቅቱ ይጠይቁት የነበሩት ደፋር የሆኑ ጥቂት ሰዎች ብቻ ነበሩ። ጳውሎስ የቀረው ጊዜ አጭር መሆኑን ተገንዝቦ ነበር። “መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫውን እስከ መጨረሻ ሮጫለሁ፤ እምነትን ጠብቄያለሁ” ብሏል። (2 ጢሞቴዎስ 4:7) ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ጳውሎስ ሰማዕት ሆኖ ሳይገደል አልቀረም። ሐዋርያው የጻፋቸው ደብዳቤዎች በዛሬው ጊዜ ለሚገኙ እውነተኛ የአምላክ አገልጋዮችም መመሪያ ይሰጣሉ።

—በሮም፤ በ1 ቆሮንቶስ፤ በ2 ቆሮንቶስ፤ በገላትያ፤ በኤፌሶን፤ በፊልጵስዩስ፤ በቆላስይስ፤ በ1 ተሰሎንቄ፤ በ2 ተሰሎንቄ፤ በ1 ጢሞቴዎስ፤ በ2 ጢሞቴዎስ፤ በቲቶ፤ በፊልሞና እና በዕብራውያን መጻሕፍት ላይ የተመሠረተ።

  • ጳውሎስ የጻፋቸው ደብዳቤዎች ሥነ ምግባርንና አኗኗርን በተመለከተ ምን ጠንከር ያለ ምክር ይዘዋል?

  • ጳውሎስ የአምላክ ዓላማ በክርስቶስ በኩል የተፈጸመበትን መንገድ በተመለከተ ብርሃን የፈነጠቀው እንዴት ነው?

  • ጳውሎስ ተገቢ የሆነውን የጉባኤ አደረጃጀት አስመልክቶ ምን መመሪያ ሰጥቷል?

ተስፋ የተሰጠበት ዘር ማን ነው?

አዳምና ሔዋን ኃጢአት ከሠሩ በኋላ አምላክ ምሳሌያዊ አነጋገር በመጠቀም እባቡን እንዲህ ብሎት ነበር፦ “በአንተና በሴቲቱ፣ በዘርህና በዘሯ መካከል፣ ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ተረከዙን ትቀጠቅጣለህ።” (ዘፍጥረት 3:15) ቅዱሳን መጻሕፍት ዲያብሎስን “የመጀመሪያው እባብ” በማለት ይጠሩታል። (ራእይ 12:9) አምላክ ተስፋ የሰጠበት ዘር ወይም አዳኝ ማንነት ሚስጥር ሆኖ ነበር፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህ ሚስጥር በጊዜ ሂደት ደረጃ በደረጃ ግልጽ ሆኗል።

አዳምና ሔዋን ኃጢአት ከሠሩ ከ2,000 ዓመታት ገደማ በኋላ ይሖዋ፣ ተስፋ የሰጠበት ዘር በአብርሃም የትውልድ ሐረግ በኩል እንደሚመጣ ገለጸ። (ዘፍጥረት 22:17, 18) ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ ደግሞ ሐዋርያው ጳውሎስ፣ የዚህ ዘር ዋነኛ ክፍል መሲሑ ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ተናገረ። (ገላትያ 3:16) በዘፍጥረት 3:15 ላይ እንደተገለጸው ኢየሱስ ሲገደል በምሳሌያዊ መንገድ “ተረከዙ” ተቀጥቅጧል። ይሁን እንጂ አምላክ፣ ኢየሱስን ከሞት በማስነሳት “መንፈስ ሆኖ ሕያው እንዲሆን” አድርጎታል።—1 ጴጥሮስ 3:18

ከዚህ በተጨማሪ አምላክ 144,000 ሰዎች የዘሩ ሁለተኛ ክፍል እንዲሆኑ የማድረግ ዓላማ ነበረው። (ገላትያ 3:29፤ ራእይ 14:1) እነዚህ ሰዎች በሰማይ በሚገኘው መንግሥት ከክርስቶስ ጋር ወራሾች እንዲሆኑ መንፈሳዊ አካል ይዘው ከሞት ይነሣሉ።—ሮም 8:16, 17

በሰማይ ላይ ኃይል ንጉሥ ሆኖ እየገዛ ያለው ኢየሱስ፣ የዲያብሎስን ዘር ማለትም ሰይጣንን የሚከተሉትን ክፉ የሆኑ የሰው ልጆችና አጋንንት በቅርቡ ያጠፋቸዋል። (ዮሐንስ 8:44፤ ኤፌሶን 6:12) ኢየሱስ በሚገዛበት ወቅት ታዛዥ የሆኑ የሰው ዘሮች በሙሉ ሰላም በሰፈነበት ሁኔታ በደስታ ይኖራሉ። ውሎ አድሮም ኢየሱስ የእባቡን “ራስ” በመቀጥቀጥ ከሕልውና ውጪ ያደርገዋል።—ዕብራውያን 2:14

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ