የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • yc ትምህርት 10 ገጽ 22-23
  • ኢየሱስ ምንጊዜም ታዛዥ ነበር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ ምንጊዜም ታዛዥ ነበር
  • ልጆቻችሁን አስተምሩ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ ታዛዥነትን ተምሯል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ማርያም ከተወችው ምሳሌ ምን ልንማር እንችላለን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • “በልቧ ታሰላስል ነበር”
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
  • “ልጄ ይህ ነው”
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
ለተጨማሪ መረጃ
ልጆቻችሁን አስተምሩ
yc ትምህርት 10 ገጽ 22-23
ዮሴፍና ማርያም፣ ትንሹን ኢየሱስን ቤተ መቅደሱ ውስጥ ሲያገኙት

ትምህርት 10

ኢየሱስ ምንጊዜም ታዛዥ ነበር

ወላጆችህን መታዘዝ ሁልጊዜ ቀላል ነው?— አንዳንድ ጊዜ ከባድ ይሆናል። ኢየሱስ፣ ይሖዋንም ሆነ ወላጆቹን ይታዘዝ እንደነበረ ታውቃለህ?— ኢየሱስ የተወው ምሳሌ ወላጆችህን መታዘዝ ቀላል በማይሆንበት ጊዜ ጭምር ታዛዥ እንድትሆን ይረዳሃል። እስቲ ስለ ኢየሱስ እንመልከት።

ኢየሱስ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት በሰማይ ከአባቱ ከይሖዋ ጋር ይኖር ነበር። ይሁን እንጂ ኢየሱስ በምድር ላይም ወላጆች ነበሩት። ወላጆቹም ዮሴፍ እና ማርያም ይባላሉ። ዮሴፍና ማርያም የኢየሱስ ወላጆች ሊሆኑ የቻሉት እንዴት እንደሆነ ታውቃለህ?—

ይሖዋ፣ ኢየሱስ በምድር ላይ እንዲወለድ ሲል የልጁን ሕይወት በማርያም ሆድ ውስጥ አስቀመጠው። ይህ ተአምር ነው! ኢየሱስ ልክ እንደማንኛውም ሕፃን በማርያም ሆድ ውስጥ አደገ። ከዘጠኝ ወር በኋላ ኢየሱስ ተወለደ። ማርያምና ዮሴፍ በምድር ላይ የኢየሱስ ወላጆች የሆኑት በዚህ መንገድ ነበር።

ኢየሱስ ገና የ12 ዓመት ልጅ ሳለ በሰማይ የሚኖረውን አባቱን ይሖዋን በጣም እንደሚወደው የሚያሳይ አንድ ነገር አደረገ። ይህ ሁኔታ የተከሰተው ኢየሱስ እና ቤተሰቡ የፋሲካን በዓል ለማክበር ረጅም መንገድ ተጉዘው ወደ ኢየሩሳሌም በሄዱበት ወቅት ነው። ወደ ቤት እየተመለሱ እያለ ዮሴፍና ማርያም፣ ኢየሱስን ቢፈልጉትም ሊያገኙት አልቻሉም። ኢየሱስ የት እንደነበር ታውቃለህ?—

ኢየሱስ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ምን እያደረገ ነበር?

ዮሴፍና ማርያም፣ በፍጥነት ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ኢየሱስን በየቦታው መፈለግ ጀመሩ። ሊያገኙት ስላልቻሉም በጣም ተጨነቁ። ከሦስት ቀን በኋላ ግን በቤተ መቅደሱ ውስጥ አገኙት! ኢየሱስ ቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበረው ለምን እንደሆነ ታውቃለህ?— በዚያ ስለ አባቱ ስለ ይሖዋ መማር ስለሚችል ነው። ይሖዋን ስለሚወድ እንዲሁም እሱን ደስ ማሰኘት የሚችለው እንዴት እንደሆነ መማር ስለሚፈልግ ነበር። ኢየሱስ አድጎ ትልቅ ሰው ከሆነም በኋላ ምንጊዜም ይሖዋን ይታዘዝ ነበር። ኢየሱስ፣ ይሖዋን መታዘዝ ከባድና ሥቃይ የሚያስከትል በሆነበት ጊዜም እንኳ አባቱን ታዝዟል። ኢየሱስ ዮሴፍና ማርያምንስ ሁልጊዜ ይታዘዝ ነበር?— አዎ፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ያደርግ እንደነበር ይናገራል።

ከኢየሱስ ምሳሌ ምን ትምህርት ታገኛለህ?— ወላጆችህን መታዘዝ ከባድ በሚሆንበት ጊዜም እንኳ ይህን ማድረግ ይኖርብሃል። ታዲያ እንዲህ ታደርጋለህ?—

የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብቡ

  • ሉቃስ 1:30-35፤ 2:45-52

  • ኤፌሶን 6:1

  • ዕብራውያን 5:8

ጥያቄዎች፦

  • ዮሴፍና ማርያም በምድር ላይ የኢየሱስ ወላጆች የሆኑት እንዴት ነው?

  • የኢየሱስ ወላጆች በኢየሩሳሌም ኢየሱስን ፈልገው ያገኙት የት ነው?

  • ከኢየሱስ ምሳሌ ምን ትምህርት ልታገኝ ትችላለህ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ