የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • jy ምዕ. 10 ገጽ 28-ገጽ 29 አን. 7
  • የኢየሱስ ቤተሰብ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የኢየሱስ ቤተሰብ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ
  • ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ወደ ኢየሩሳሌም የተደረጉ ጉዞዎች
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • ኢየሱስ በአሥራ ሁለት ዓመቱ
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ወጣቱ ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ውስጥ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ኢየሱስ ታዛዥነትን ተምሯል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
ለተጨማሪ መረጃ
ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
jy ምዕ. 10 ገጽ 28-ገጽ 29 አን. 7
ኢየሱስ በአሥራ ሁለት ዓመቱ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ለአይሁድ መምህራን ጥያቄ ሲያቀርብ

ምዕራፍ 10

የኢየሱስ ቤተሰብ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ

ሉቃስ 2:40-52

  • የ12 ዓመቱ ኢየሱስ ለመምህራኑ ጥያቄ አቀረበ

  • ኢየሱስ ይሖዋን “አባቴ” ብሎ ጠራው

ጸደይ ደርሷል። በዚህ ወቅት ዮሴፍና ቤተሰቡ ከወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር ሆነው በየዓመቱ ወደ ኢየሩሳሌም ይጓዛሉ። ወደዚያ የሚሄዱት ሕጉ በሚያዘው መሠረት ፋሲካን ለማክበር ነው። (ዘዳግም 16:16) ከናዝሬት ተነስቶ ኢየሩሳሌም ለመድረስ 120 ኪሎ ሜትር ገደማ መጓዝ ይጠይቃል። ይህ ወቅት እንቅስቃሴ የበዛበትና አስደሳች ነው። የ12 ዓመቱ ኢየሱስ በዓሉን እንዲሁም ወደ ቤተ መቅደሱ በድጋሚ የሚሄድበትን ጊዜ በጉጉት እየተጠባበቀ ነው።

ለኢየሱስና ለቤተሰቡ ፋሲካ የአንድ ቀን በዓል አይደለም። የፋሲካ ማግስት፣ ሰባት ቀን የሚወስደው ‘የቂጣ በዓል የሚከበርበት የመጀመሪያ ቀን’ ነው። (ማርቆስ 14:1) ይህ በዓል፣ የፋሲካ በዓል ክፍል እንደሆነ ተደርጎ ይታያል። ቤተሰቡ ናዝሬት ከሚገኘው መኖሪያቸው ተነስተው የሚያደርጉት ጉዞ፣ ኢየሩሳሌም የሚቆዩባቸው ቀናት እና የመልስ ጉዞው በአጠቃላይ ሁለት ሳምንት ገደማ ይወስዳል። ሆኖም በዚህ ዓመት ከኢየሱስ ጋር የተያያዘ አንድ ሁኔታ በመከሰቱ ምክንያት ጉዞው ከዚህ የበለጠ ጊዜ ወስዶባቸዋል። ሁኔታው የታወቀው ከኢየሩሳሌም ተነስተው ጉዞ ከጀመሩ በኋላ ነው።

አስደሳች ጉዞዎች

ኢየሱስና ቤተሰቡ ወደ ኢየሩሳሌም ሲጓዙ

ሦስቱን ዓመታዊ በዓላት ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም የሚደረጉት ጉዞዎች አስደሳች ነበሩ። (ዘዳግም 16:15) በዚህ ጉዞ ላይ ኢየሱስ የተለያዩ የአገሪቱን ክፍሎች ለማየት፣ ስለ መልከአ ምድሩ ለማወቅና ከሌሎች አካባቢዎች ከሚመጡ የእምነት ባልንጀሮቹ ጋር ለመተዋወቅ አጋጣሚ ያገኛል። እነዚያ ጉዞዎች አስደሳች ትዝታ ትተው የሚያልፉ ነበሩ!

ዮሴፍና ማርያም፣ ኢየሱስ ወደ ሰሜን አብረዋቸው ከሚጓዙት ወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር መስሏቸዋል። ሆኖም ምሽት ላይ ሲያርፉ ኢየሱስን ሊያገኙት አልቻሉም። በመሆኑም አብረዋቸው በሚጓዙት ሰዎች መካከል ፈለጉት፤ እሱ ግን እዚያ የለም። ልጃቸው ሊገኝ አልቻለም! ስለዚህ ዮሴፍና ማርያም እሱን ለመፈለግ እንደገና ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

ቀኑን ሙሉ ቢፈልጉትም ሊያገኙት አልቻሉም። በሁለተኛውም ቀን አልተገኘም። በመጨረሻም በሦስተኛው ቀን ልጃቸውን ቤተ መቅደሱ ውስጥ አገኙት። ከቤተ መቅደሱ በርካታ አዳራሾች በአንዱ ውስጥ በአይሁድ መምህራን መካከል ተቀምጧል። ኢየሱስ መምህራኑን እያዳመጠና እየጠየቃቸው ነው፤ እነሱም በመረዳት ችሎታው ተደንቀዋል።

ዮሴፍና ማርያም ኢየሱስን አገኙት

ማርያም “ልጄ፣ ምነው እንዲህ አደረግከን? እኔና አባትህ እኮ በጣም ተጨንቀን ስንፈልግህ ነበር” ስትል ጠየቀችው።—ሉቃስ 2:48

ኢየሱስ ግን የት ሊያገኙት እንደሚችሉ ባለማወቃቸው ተገረመ። “ለምን ፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት መሆን እንደሚገባኝ አታውቁም?” አላቸው።—ሉቃስ 2:49

ኢየሱስ ከወላጆቹ ጋር ከተገናኘ በኋላ በናዝሬት ወደሚገኘው ቤታቸው አብሯቸው ተመለሰ፤ እንደ ወትሮውም ለወላጆቹ መገዛቱን ቀጠለ። በአካልና በጥበብ እያደገ ሄደ። ገና ልጅ ቢሆንም እንኳ በአምላክና በሰው ፊት ሞገስ አግኝቷል። በእርግጥም ኢየሱስ ከልጅነቱ ጀምሮ መንፈሳዊ ነገሮችን በመከታተል ብቻ ሳይሆን ለወላጆቹ አክብሮት በማሳየት ረገድም ጥሩ ምሳሌ ትቷል።

  • ኢየሱስ በጸደይ ወራት ከቤተሰቡ ጋር አዘውትሮ ወዴት ይጓዛል? ለምንስ?

  • ኢየሱስ የ12 ዓመት ልጅ ሳለ ዮሴፍና ማርያም ከኢየሩሳሌም ሲመለሱ ምን ተገነዘቡ? ኢየሱስን የት አገኙት?

  • ኢየሱስ በዛሬው ጊዜ ላሉት ወጣቶች ምን ግሩም ምሳሌ ትቷል?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ