የርዕስ ማውጫ
ክፍል 1 ወደ ይሖዋ ተመለስ—ለምን?
በጥንት ዘመን የኖሩ የይሖዋ ሕዝቦች እኛ የሚደርሱብን ዓይነት ችግሮች አጋጥመዋቸዋል። ይሖዋ ቅድሚያውን በመውሰድ እነዚህን አገልጋዮቹን ረድቷቸዋል፤ ለእኛም ተመሳሳይ ነገር እንደሚያደርግልን ቃል ገብቷል። ይሖዋ አሳቢና አፍቃሪ እረኛ ስለሆነ የጠፉ በጎቹን ይፈልጋል፤ ወደ እሱ እንዲመለሱም ይጋብዛቸዋል።
ከክፍል 2-4 መመለስ ፈታኝ እንዲሆን የሚያደርጉ አንዳንድ ነገሮች
ታማኝ የሆኑ የአምላክ አገልጋዮች እንኳ በጭንቀት የተዋጡበት፣ ስሜታቸው የተጎዳበትና የበደለኝነት ስሜት የተሰማቸው ጊዜ ነበር፤ ይህ ደግሞ በመንፈሳዊ እንቅስቃሴያቸው ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል። ወደ ቀድሞ አቋማቸው እንዲመለሱ፣ እንደገና ከሕዝቡ ጋር እንዲቀራረቡና ደስታቸውን መልሰው እንዲያገኙ ይሖዋ የረዳቸው እንዴት እንደሆነ እንድትመረምር እንጋብዝሃለን።
ክፍል 3 የስሜት መጎዳት—‘ቅር የተሰኘንበት ነገር’ ሲኖር
ክፍል 4 የበደለኝነት ስሜት—‘ከኃጢአቴ አንጻኝ’
ክፍል 5 ወደ ይሖዋ ተመለስ—እንዴት?
ይሖዋ ወደ እሱ እንድትመለስ እንደሚፈልግ የሚያሳየውን ማስረጃ መርምር። አንዳንድ ክርስቲያኖች ወደ ይሖዋ የተመለሱት፣ ጉባኤው የተቀበላቸው እንዲሁም እንደቀድሞው በቅንዓት እንዲያገለግሉ ሽማግሌዎች የረዷቸው እንዴት ነው?