የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 99 ገጽ 230-ገጽ 231 አን. 4
  • አንድ የእስር ቤት ጠባቂ ክርስቲያን ሆነ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አንድ የእስር ቤት ጠባቂ ክርስቲያን ሆነ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “ወደ መቄዶንያ ተሻገር”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
  • ሲላስ የማበረታቻ ምንጭ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • “ከመረዳት ችሎታ ሁሉ በላይ የሆነው የአምላክ ሰላም”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • ጽኑ እምነት በመያዝ ምሥራቹን መስበክ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 99 ገጽ 230-ገጽ 231 አን. 4
በፊልጵስዩስ የሚኖረው የእስር ቤት ጠባቂ የእስር ቤቱ በሮች ተከፍተው ቢያገኛቸውም አንድም እስረኛ አላመለጠም

ትምህርት 99

አንድ የእስር ቤት ጠባቂ ክርስቲያን ሆነ

በፊልጵስዩስ የምትኖር ጋኔን የያዛት አንዲት አገልጋይ ነበረች። እሷም ጋኔኑ እንድትጠነቁል ወይም ወደፊት ስለሚሆነው ነገር እንድትናገር ያደርጋት ስለነበር ለጌቶቿ ብዙ ገንዘብ ታስገኝላቸው ነበር። ጳውሎስና ሲላስ ወደ ፊልጵስዩስ ከመጡ በኋላ ለብዙ ቀናት ትከተላቸው ነበር። ‘እነዚህ ሰዎች የልዑሉ አምላክ ባሪያዎች ናቸው’ እያለች ትጮኽ ነበር። በመጨረሻም ጳውሎስ ጋኔኑን ‘ከእሷ እንድትወጣ በኢየሱስ ስም አዝሃለሁ!’ አለው። በዚህ ጊዜ ጋኔኑ ከእሷ ወጣ።

የዚህች አገልጋይ ጌቶች ከዚያ በኋላ እየጠነቆለች ገንዘብ እንደማታመጣላቸው ሲያውቁ በጣም ተናደዱ። በመሆኑም ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው ወደ ከተማዋ ሕግ አስከባሪዎች ወሰዷቸውና እንዲህ አሉ፦ ‘እነዚህ ሰዎች ሕግ አያከብሩም፤ ደግሞም መላ ከተማዋን እየረበሹ ነው።’ የከተማዋ ሕግ አስከባሪዎችም ጳውሎስና ሲላስ እንዲገረፉና እስር ቤት እንዲገቡ አዘዙ። የእስር ቤቱ ጠባቂም ጨለማ ወደሆነው የእስር ቤቱ ውስጠኛ ክፍል ወስዶ በእግር ግንድ አሰራቸው።

ጳውሎስና ሲላስ ግን ሌሎቹ እስረኞች እየሰሟቸው ይሖዋን በመዝሙር ያወድሱ ነበር። እኩለ ሌሊት ላይ በድንገት ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ እስር ቤቱን ከላይ እስከ ታች አናወጠው። የእስር ቤቱ በሮች ተከፈቱ፤ እስረኞቹ የታሰሩባቸው ሰንሰለቶችም ተፈቱ። የእስር ቤቱ ጠባቂ ወደ እስር ቤቱ ውስጠኛ ክፍል እየሮጠ ሲመጣ በሮቹ መከፈታቸውን አየ። እስረኞቹ በሙሉ ያመለጡ ስለመሰለው ራሱን ለመግደል ሰይፍ መዘዘ።

በዚህ ጊዜ ጳውሎስ ‘በራስህ ላይ ጉዳት አታድርስ! ሁላችንም አለን!’ አለው። የእስር ቤቱ ጠባቂም በፍጥነት ሄዶ በጳውሎስና በሲላስ ፊት ተንበረከከ። ከዚያም “ለመዳን ምን ማድረግ ይኖርብኛል?” በማለት ጠየቃቸው። እነሱም ‘አንተም ሆንክ ቤተሰብህ በኢየሱስ ማመን አለባችሁ’ አሉት። ከዚያም ጳውሎስና ሲላስ ለእስር ቤቱ ጠባቂና ለቤተሰቦቹ የይሖዋን ቃል አስተማሯቸው፤ እነሱም ወዲያውኑ ተጠመቁ።

“ሰዎች ይይዟችኋል፤ ስደት ያደርሱባችኋል እንዲሁም ለምኩራብና ለወህኒ ቤት አሳልፈው ይሰጧችኋል። በስሜም ምክንያት በነገሥታትና በገዢዎች ፊት ያቀርቧችኋል። ይህም ለመመሥከር የሚያስችል አጋጣሚ ይከፍትላችኋል።”—ሉቃስ 21:12, 13

ጥያቄ፦ ጳውሎስና ሲላስ የታሰሩት ለምንድን ነው? የእስር ቤቱ ጠባቂ እውነትን የተማረው እንዴት ነው?

የሐዋርያት ሥራ 16:16-34

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ