የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ልብ ብላችሁ አዳምጡ፦
በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ እምነት ማሳየታችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (ማር. 11:22)
ይሖዋን አስመልክቶ በተነገሩ ዘይቤያዊ አገላለጾች ላይ ማሰላሰል ምን ጥቅሞች አሉት? (መዝ. 28:7፤ ሉቃስ 11:11-13፤ ዘዳ. 32:4፤ መዝ. 23:1)
እምነታችንን ማጠናከር የምንችለው እንዴት ነው? (ማር. 9:24)
‘በቀላሉ ተብትቦ የሚይዘን ኃጢአት’ ምንድን ነው? ራሳችንን ከዚህ ኃጢአት መጠበቅ የምንችለውስ እንዴት ነው? (ዕብ. 12:1)
እውነተኛ እምነት ያላቸው ሰዎች ወሮታ እንደሚያገኙ እርግጠኛ እንድንሆን የሚያደርገን ምንድን ነው? (ዕብ. 11:6)