የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • th ጥናት 18 ገጽ 21
  • ግንዛቤ የሚያሰፋ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ግንዛቤ የሚያሰፋ
  • ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በጋለ ስሜት መናገር
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ግንዛቤ የሚያሰፋ
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • የአድማጮችን ልብ ለመንካት መጣር
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • የትምህርቱን ጥቅም ግልጽ ማድረግ
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
ለተጨማሪ መረጃ
ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
th ጥናት 18 ገጽ 21

ጥናት 18

ግንዛቤ የሚያሰፋ

ጥቅስ

1 ቆሮንቶስ 9:19-23

ፍሬ ሐሳብ፦ አድማጮችህ ርዕሰ ጉዳዩን እንዲያስቡበት ብሎም ጠቃሚ ትምህርት እንዳገኙ እንዲሰማቸው በሚያደርግ መንገድ ትምህርቱን ለማቅረብ ጥረት አድርግ።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • አድማጮችህ ስለ ጉዳዩ ያላቸውን እውቀት ግምት ውስጥ አስገባ። ከዚህ በፊት የሚያውቋቸውን ነገሮች እንዲሁ ከመድገም ይልቅ ርዕሰ ጉዳዩን ከሌላ አቅጣጫ እንዲመለከቱት እርዳቸው።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    አድማጮች የሚያውቋቸውን ነጥቦች ስትጠቅስ ፈጠን ልትል ትችላለህ። አዲስ የሆነ ሐሳብ በምትጠቅስበት ጊዜ ግን ረጋ ብለህ ተናገር።

  • ምርምር አድርግ እንዲሁም አሰላስል። ቁልፍ የሆኑ ነጥቦችን ለማስረዳት፣ አድማጮች ብዙም የማያውቋቸውን መረጃዎች ወይም ወቅታዊ ሁኔታዎች ጥቀስ። ስለምታቀርበው ትምህርት እንዲሁም በርዕሰ ጉዳዩና በምትጠቅሳቸው መረጃዎች መካከል ስላለው ዝምድና በጥሞና አስብ።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    ትምህርቱን ስትዘጋጅ ‘ምን? ለምን? መቼ? የት? ማን? እና እንዴት?’ የሚሉትን ጥያቄዎች እያነሳህ ስለ ጉዳዩ በጥልቀት ማሰብ ይኖርብሃል። ንግግር በምትሰጥበት ጊዜ ከእነዚህ ጥያቄዎች አንዳንዶቹን በማንሳትና መልስ በመስጠት ትምህርቱን ሕያው አድርገህ ማቅረብ ትችላለህ።

  • የትምህርቱን ጠቀሜታ አጉላ። ከመጽሐፍ ቅዱስ የምትጠቅሳቸው ሐሳቦች አድማጮችን በዕለታዊ ሕይወታቸው እንዴት ሊጠቅሟቸው እንደሚችሉ ግለጽ። ከአድማጮችህ ሕይወት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሁኔታዎች፣ አመለካከቶችና ድርጊቶች እንደ ምሳሌ በመጥቀስ ትምህርቱን አብራራ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ