ተግሣጽ
መጽሐፍ ቅዱስ ከሁሉ የላቀ የተግሣጽ ምንጭ የሆነው ለምንድን ነው?
ሁላችንም መመሪያና እርማት የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?
የይሖዋ ተግሣጽ ለምን ነገር ማስረጃ ነው?
በተጨማሪም ዘዳ 8:5፤ ምሳሌ 13:24፤ ራእይ 3:19ን ተመልከት
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
2ሳሙ 12:9-13፤ 1ነገ 15:5፤ ሥራ 13:22—ንጉሥ ዳዊት በጣም ከባድ ኃጢአቶች ቢሠራም ይሖዋ በፍቅር ተግሣጽ ሰጥቶታል እንዲሁም ይቅር ብሎታል
ዮናስ 1:1-4, 15-17፤ 3:1-3—ነቢዩ ዮናስ የተሰጠውን ኃላፊነት ላለመወጣት ሸሽቶ በመሄዱ ይሖዋ ገሥጾታል፤ ሆኖም ሁለተኛ ዕድል ሰጥቶታል
የአምላክን ተግሣጽ አቅልለን አለመመልከታችን ጥበብ የሆነው ለምንድን ነው?
ምሳሌ 9:8፤ 12:1፤ 17:10፤ ዕብ 12:5, 6
በተጨማሪም 2ዜና 36:15, 16ን ተመልከት
የአምላክን ተግሣጽ የማይቀበሉ ሰዎች ምን ይገጥማቸዋል?
ምሳሌ 1:24-26፤ 13:18፤ 15:32፤ 29:1
በተጨማሪም ኤር 7:27, 28, 32-34ን ተመልከት
የይሖዋን ተግሣጽ መስማት ምን ጥቅም ያስገኛል?
ምሳሌ 4:13፤ 1ቆሮ 11:32፤ ቲቶ 1:13፤ ዕብ 12:10, 11
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ዘዳ 30:1-6—ነቢዩ ሙሴ፣ ይሖዋ ለሕዝቡ የሚሰጠውን ተግሣጽ የሚሰሙ ሁሉ ምን በረከት እንደሚያገኙ ትንቢት ተናግሯል
2ዜና 7:13, 14—ይሖዋ፣ መለኮታዊ ተግሣጽ መቀበል ምን ጥሩ ውጤቶች እንዳሉት ለንጉሥ ሰለሞን ነግሮታል
ለሌሎች ከተሰጠ ተግሣጽ መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው?
ሌሎች ከበድ ያለ ተግሣጽ ሲሰጣቸው መደሰት የሌለብን ለምንድን ነው?
አምላክ ከሚሰጠው ተግሣጽና ምክር ጥቅም ለማግኘት ምን ማድረግ ይኖርብናል?
በተጨማሪም ዘዳ 17:18, 19፤ መዝ 119:97ን ተመልከት
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
1ዜና 22:11-13—ንጉሥ ዳዊት፣ ልጁ ሰለሞን የአምላክን መመሪያዎች በጥንቃቄ እስከተከተለ ድረስ በረከት እንደሚያገኝ አስረግጦ ነግሮታል
መዝ 1:1-6—ይሖዋ ቃሉን የሚያነብቡና የሚያሰላስሉበት ሰዎች እንደሚባረኩ ቃል ገብቷል
አፍቃሪ ወላጆች ልጆቻቸውን የሚገሥጹት ለምንድን ነው?
“ወላጆች” የሚለውን ተመልከት
ልጆች ወላጆቻቸው ተግሣጽ ሲሰጧቸው ምን ማድረግ ይኖርባቸዋል?
“ቤተሰብ—ወንዶች እና ሴቶች ልጆች” የሚለውን ተመልከት