ታዛዥነት
ታዛዥነት ምን ያህል አስፈላጊ ነው?
ዘፀ 19:5፤ ዘዳ 10:12, 13፤ መክ 12:13፤ ያዕ 1:22
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
1ሳሙ 15:17-23—ነቢዩ ሳሙኤል፣ የይሖዋን ትእዛዝ በመጣሱ ንጉሥ ሳኦልን ገሥጾታል፤ ከዚያም ሳሙኤል የታዛዥነትን አስፈላጊነት አበክሮ ነግሮታል
ዕብ 5:7-10—ኢየሱስ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊትም ፍጹም የአምላክ ልጅ ነው፤ ሆኖም ምድር ላይ ከደረሰበት መከራ መታዘዝን ተምሯል
አንድ ክርስቲያን፣ አንድ ባለሥልጣን የይሖዋን ትእዛዝ እንዲጥስ ቢጠይቀው ምን ማድረግ ይኖርበታል?
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ዳን 3:13-18—ሦስት ታማኝ ዕብራውያን፣ ሕይወታቸውን ሊያሳጣቸው እንደሚችል ቢያውቁም ንጉሥ ናቡከደነጾር ላቆመው ምስል ለመስገድ ፈቃደኛ አልሆኑም
ማቴ 22:15-22—ኢየሱስ፣ ተከታዮቹ የመንግሥት ባለሥልጣናትን የሚታዘዙት የይሖዋን ትእዛዝ የሚያስጥስ ነገር እስካልጠየቋቸው ድረስ እንደሆነ ተናግሯል
ሥራ 4:18-31—ሐዋርያት መስበካቸውን እንዲያቆሙ ሥልጣን ላይ ካሉ ሰዎች ቢነገራቸውም በድፍረት መስበካቸውን ቀጥለዋል
ምንጊዜም ለይሖዋ ታዛዥ ለመሆን ምን ማድረግ አለብን?
ዘዳ 6:1-5፤ መዝ 112:1፤ 1ዮሐ 5:2, 3
በተጨማሪም መዝ 119:11, 112፤ ሮም 6:17ን ተመልከት
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ዕዝራ 7:7-10—ታማኙ ካህን ዕዝራ፣ ግንባር ቀደም ሆኖ የአምላክን ሕግ መታዘዝ እንዲሁም ለሌሎች ማስተማር እንዲችል ልቡን አዘጋጅቷል
ዮሐ 14:31—ኢየሱስ ልክ አባቱ እንዳዘዘው የሚያደርገው ለምን እንደሆነ ተናግሯል
ይሖዋንና ኢየሱስን ለመታዘዝ የሚያነሳሳን ምንድን ነው?
መታዘዝ የእምነታችንን መጠን የሚያሳየው እንዴት ነው?
በተጨማሪም ዘዳ 9:23ን ተመልከት
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ዘፍ 6:9-22፤ ዕብ 11:7—ኖኅ፣ ይሖዋ መርከብ እንዲሠራ ባዘዘው መሠረት “ልክ እንደዚሁ” በማድረግ እምነቱን አሳይቷል
ዕብ 11:8, 9, 17—አብርሃም ዑርን ለቅቆ እንዲወጣ ብቻ ሳይሆን የገዛ ልጁን መሥዋዕት እንዲያደርግ ይሖዋ የሰጠውን ትእዛዝ በመጠበቅ እምነት እንዳለው አሳይቷል
ይሖዋ ታዛዥነትን የሚባርከው እንዴት ነው?
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ዘሌ 26:3-6—ይሖዋ እሱን የሚታዘዙትን እንደሚባርካቸውና እንደሚንከባከባቸው ቃል ገብቷል
ዘኁ 13:30, 31፤ 14:22-24—ካሌብ የታዛዥነት መንፈስ አሳይቷል፤ በመሆኑም ይሖዋ ባርኮታል
አለመታዘዝ ምን ያስከትላል?
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ዘፍ 2:16, 17፤ 3:17-19—አዳምና ሔዋን ይሖዋን ባለመታዘዛቸው ከገነት ተባረሩ፤ ፍጽምናቸውንና የዘላለም ሕይወት አጡ
ዘዳ 18:18, 19፤ ሥራ 3:12, 18, 22, 23—ይሖዋ፣ ከሙሴ የሚበልጥ ነቢይ እንደሚነሳ ትንቢት በተናገረበት ወቅት ይህን ነቢይ አለመታዘዝ ከባድ መዘዝ እንደሚያስከትል ጠቁሟል
ይሁዳ 6, 7—የዓመፀኞቹ መላእክት እንዲሁም የሰዶምና ገሞራ ነዋሪዎች አለመታዘዝ የይሖዋን ቁጣ ቀስቅሶታል
ኢየሱስ ክርስቶስን መታዘዝ ያለብን ለምንድን ነው?
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ዮሐ 12:46-48፤ 14:24—ኢየሱስ የእሱን ቃል የማይታዘዙ ሰዎች እንደሚፈረድባቸው ተናግሯል
ክርስቲያኖች በጉባኤ ውስጥ ለበላይ ተመልካቾች መታዘዝ ያለባቸው ለምንድን ነው?
ክርስቲያን ሚስት ለባሏ መገዛት ያለባት ለምንድን ነው?
ልጆች ለወላጆቻቸው የሚታዘዙት ለምንድን ነው?
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ዘፍ 37:3, 4, 8, 11-13, 18—ወጣቱ ዮሴፍ ወንድሞቹ እንደሚጠሉት እያወቀም አባቱ ወደ እነሱ እንዲሄድ የሰጠውን ትእዛዝ አክብሯል
ሉቃስ 2:51—ፍጹም የሆነው ኢየሱስ፣ ፍጹም ላልሆኑት ወላጆቹ ለዮሴፍና ለማርያም ሁልጊዜ ይገዛላቸው ነበር