አምልኮ
ሊመለክ የሚገባው ማን ብቻ ነው?
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ማቴ 4:8-10—ሰይጣን፣ ኢየሱስ አንድ ጊዜ ካመለከው የዓለምን መንግሥታት ሁሉ እንደሚሰጠው ቃል ገባለት፤ ኢየሱስ ግን ግብዣውን አልተቀበለም፤ መመለክ ያለበት ይሖዋ ብቻ እንደሆነ ተናገረ
ራእይ 19:9, 10—አንድ ኃያል መልአክ፣ ሐዋርያው ዮሐንስ አምልኮ አከል ክብር እንዲሰጠው አልፈቀደለትም
ይሖዋ እንድናመልከው የሚፈልገው እንዴት ነው?
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ኢሳ 1:10-17—ይሖዋ፣ የእሱን መሥፈርቶች ለመከተል አሻፈረኝ ያሉ ግብዝ ሰዎች የሚያቀርቡለትን የአምልኮ ሥርዓቶች አይቀበልም እንዲሁም ይጸየፋቸዋል
ማቴ 15:1-11—ይሖዋ በወግ ላይ የተመሠረተ አምልኮን እንደማይቀበል ኢየሱስ ተናግሯል፤ ምክንያቱም እንዲህ ያለው አምልኮ ሰዎች ያወጧቸውን ደንቦች ከአምላክ ሕጎች ያስቀድማል
የሚቻል በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ ይሖዋን ማምለክ ያለብን ከማን ጋር ነው?
በተጨማሪም መዝ 133:1-3ን ተመልከት
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ሥራ 2:40-42—በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች ለጸሎት፣ አብረው ጊዜ ለማሳለፍና በመንፈስ መሪነት የተጻፉ ትምህርቶችን አብረው ለማጥናት ይሰበሰቡ ነበር
1ቆሮ 14:26-40—ሐዋርያው ጳውሎስ የጉባኤ ስብሰባዎች ሥርዓታማና የሚያንጹ እንዲሆኑ መመሪያ ሰጥቷል፤ ዓላማውም ስብሰባው ላይ የተገኙት ሁሉ እንዲማሩና የሚተላለፈውን ትምህርት እንዲረዱ ነው
አምልኳችን በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ምን ማድረግ አለብን?
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ዕብ 11:6—ሐዋርያው ጳውሎስ ይሖዋን ተቀባይነት ባለው መንገድ ለማምለክ እምነት የግድ አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል
ያዕ 2:14-17, 24-26—የኢየሱስ ወንድም የሆነው ያዕቆብ፣ እምነታችን በሥራ የተደገፈ መሆን እንዳለበት ተናግሯል፤ ለተግባር የሚያነሳሳን እምነታችን ነው