የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 1/1 ገጽ 30
  • አንድ ትንሽ ጽሑፍ በመንገድ ላይ አገኘ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አንድ ትንሽ ጽሑፍ በመንገድ ላይ አገኘ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 1/1 ገጽ 30

አንድ ትንሽ ጽሑፍ በመንገድ ላይ አገኘ

ዓመቱ 1921 ነበር። የደቡብ አፍሪካ ክፍለ ሀገር በሆነው የትራንስቫል ከፍተኛ ቦታዎች በተዘረጋው የባቡር ሐዲድ ላይ የመንገድ ጥገና ሠራተኞች ቡድን መንገድ ይሠሩ ነበር። ስሙ ክርስቲያን ቬንተር የሚባል አፍሪካነር የተባለው ጎሣ ወገን የሆነ የቡድኑ ተቆጣጣሪ አንድ ትንሽ ጽሑፍ በሐዲዱ መሃል ተወትፎ ተመለከተ። ጽሑፉ በመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስና የትናንሽ ጽሑፎች መኅበር የታተመ ነበር።

ክርስቲያን ሰዎቹ ሥራ እንዲያቆሙ አዘዘና ጽሑፉን በታላቅ ጉጉት አነበበው። አብረሃም ሴሊየርስ የሚባለውን የልጁን ባል ሊያገኘው ሮጦ ሄደና በታላቅ የደስታ ስሜት “አብረሃም፣ እኔ ዛሬ እውነትን አገኘሁ” አለው።

ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ ጽሑፉ አታሚዎች ደብዳቤ ጻፉ። በምላሹም የደቡብ አፍሪካው የመጠበቂያ ግንብ ማህበር ቅርንጫፍ ቢሮ ተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን ላከላቸው። ሁለቱም ሰዎች በምሳ እረፍታቸውና ሌሊቱን አብረው አጠኑት። ወዲያውኑ እውነትን ለጓደኞቻቸውና ለእንግዶች ማካፈል ጀመሩ።

በመጨረሻም ክርስቲያንና አብረሃም ሁለቱም ራሳቸውን ለይሖዋ የወሰኑ ምሥክሮች ሆኑ። ቅንዓታቸውና ታማኝነታቸውም ብዙ ደቡብ አፍሪካውያን እውነትን እንዲያውቁ አስችሏል። ከዚህም በተጨማሪ ከመቶ በላይ የሆኑ ተወላጆቻቸው በአሁኑ ጊዜ ንቁ የይሖዋ ምሥክሮች ናቸው! ከእነሱም አንዱ በብሩክሊን ኒውዮርክ በሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ዋና መሥሪያ ቤት እያገለገለ ሲሆን ሌላውም በደቡብ አፍሪካ የመጠበቂያ ግንብ ማህበር ቢሮዎች ያገለግላል።

ዛሬ ሰባ ዓመታት ካለፉ በኋላም ቢሆን ትናንሽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች የመንግሥቱን መልእክት ለማሰራጨት ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን ቀጥለዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ