የሕዝበ ክርስትና ቅዱስ ሥፍራዎች ምን ይደርስባቸዋል?
በአርኪዎሎጂቱ (የመሬት ቁፋሮ ተመራማሪው) አስቲዎርት ፔሮውን የተደረሰው የሕዝበ ክርስትና ቅዱስ ሥፍራዎች የተሰኘው መጽሐፍ አሳታሚዎች “ከማንኛውም የክርስትና ባሕል የመጣ ማንኛውም ሰው በኢየሩሳሌም የትንሣኤ ቤተክርስቲያን በተሠራበት በጐልጐታ (ወይም በቅዱስ መቃብር ቤተክርስቲያን) ላይ ሲቆም ከፍተኛ አድናቆት ይሰማዋል። ምክንያቱም የሕዝበ ክርስትና እምብርት ይህ ቅድስና የተሰጠውና ለዘመናት ብዙ ውጊያ የተካሄደበት ቦታ ነው” ብለዋል።
ይህ ቤተክርስቲያን ኢየሱስ ክርስቶስ በሞተበት ቦታ ላይ እንደተገነባ ለማረጋገጥ የቻለ ሰው የለም። እንዲያውም የሮማው ንጉሠ ነገሥት ቆስጠንጢኖስ በዚህ ቦታ ላይ ቤተክርስቲያን ለመሥራት ከመወሰኑ በፊት የአረማውያን ቤተመቅደስ ይገኝበት ነበር። ከዚህም በላይ ኢየሱስ “እግዚአብሔር መንፈስ ነው። የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል” ብሏል። (ዮሐንስ 4:24) እንዲህ ዓይነቶቹ አምላኪዎች ግዑዝ ለሆኑ “ቅዱስ” ቦታዎች ቅድስና አይሰጡም።
በአንድ ወቅት ኢየሩሳሌም የአምላክ ቤተመቅደስ የሚገኝባት ስፍራ ስለነበረች የንጹሕ አምልኮ ማዕከል ሆና ነበር። ይሁን እንጂ በከተማይቱ ነዋሪዎች ክህደት ምክንያት ኢየሱስ እንደተነበየው ይሖዋ ትቷታል። (ማቴዎስ 23:37, 38) ኢየሱስ ብዙዎች እንደ ቅዱስ ሥፍራ የሚመለከቱ ሃይማኖታዊ ሥፍራ እንደሚጠፋ ተንብዮአል። ሮማውያን በ70 እዘአ ኢየሩሳሌምንና ቤተ መቅደሷን ባጠፉ ጊዜ የእሱ ትንቢታዊ ቃላት ተፈጽመዋል።—ማቴዎስ 24:15, 21
የኢየሱስ ትንቢት በጠቅላላው የሕዝበ ክርስትና ሃይማኖታዊ ግዛት ላይም ከፍተኛ ፍጻሜውን ያገኛል። ሕዝበ ክርስትናና የእሷ ቅዱስ ሥፍራዎች “የጥፋት ርኩሰት” ተብሎ በተጠራው ጸረ-ሃይማኖት ኃይል ጥፋት ይደርስባቸዋል። (ዳንኤል 11:31) የይሖዋ ምሥክሮች ይህ አስደንጋጭ ሁኔታ እንዴት እንደሚፈጸም ተጨማሪ መረጃ ይሰጣሉ።
[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
በቅዱስ መቃብር ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኝ የጸሎት ቤት
[የሥዕሉ ምንጭ]
Pictorial Archive (Near Eastern History) Est.