የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 3/1 ገጽ 32
  • “የይሖዋ ምሥክሮች?”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “የይሖዋ ምሥክሮች?”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 3/1 ገጽ 32

“የይሖዋ ምሥክሮች?”

ከላይ ያለው ጥያቄ የሄልስንኪ ዩኒቨርሲቲ ቡለቲን በተሰኘ መጽሔት ላይ አርእስት ሆኖ በፊንላንድ ቋንቋ የወጣ ነበር። በርዕሱ ሥር በፕሮፌሰር ጆርማ ፓሎ የተጻፈ ደብዳቤ ሰፍሮአል። ደብዳቤው በከፊል እንዲህ ይል ነበር፦ “በቡለቲኑ ሽፋን ላይ የታተመውን የዩኒቨርሲቲያችንን ማህተም አትኩሬ መረመርኩ። ከማህተሙ አናት ላይ መሃል ለመሃል አንድ የዕብራይስጥ ጽሑፍ አገኘሁና የራሴ እንግዳ የሆነ አንድ አይሁዳዊ ምሁር ይህ ጽሑፍ ምን እንደሆነ እንዲነግረኝ ጠየቅሁት። ይህ ምሁር ዕብራይስጥ የሚያውቅ ስለነበረ ይህ ቃል በፊንላንድ ቋንቋ ‘ይሖዋ’ ማለት መሆኑን ገለጸልኝ።”

በዚህ የፊንላንድ ዩኒቨርሲቲ ማህተም ላይ የአምላክ የግል ስም መገኘቱ አንዳንድ ሰዎችን አስደንቋቸዋል። የሆነ ሆኖ ዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመ 350 ዓመት የሆነው ቢሆንም ዩኒቨርሲቲው በተቋቋመበት ዘመን ይሖዋ የሚለው ስም በአውሮፓ በሙሉ በሠፊው ይታወቅና ይሠራበት ነበር። ይህ ስም ቁጥር ስፍር በሌላቸው በዚያ ዘመን የነበሩ ሕዝባዊ ሕንፃዎች፣ ሳንቲሞችና ማህተሞች ላይ ይገኛል።—ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊ ስም የተሰኘውን ብሮሹር ተመልከቱ።

በዚህ በእኛ መቶ ዓመት ሕዝበክርስትና በአምላክ ስም ፈጽሞ ስለማትጠቀምበት ይህ ስም ይሰጠው የነበረው ትልቅ ግምት ዛሬ በአብዛኛው ተረስቷል። ዛሬ “በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ” ከሚለው የጌታ ጸሎት የመጀመሪያ ልመና ጋር በመስማማት በዚህ መለኮታዊ ስም በአምልኮቱ የሚጠቀምበትና በሠፊው የሚያሳውቅ አንድ ቡድን ብቻ ነው። (ማቴዎስ 6:9) ይህ ስም በዩኒቨርሲቲው ማህተም ላይ መኖሩ በታወቀበት ጊዜ ወዲያውኑ ወደ ሰዎች አእምሮ የመጡት የይሖዋ ምሥክሮች የሆኑት በዚህ ምክንያት ነው።

[በገጽ 32 ላይ የሚገኘው ሥዕል ምንጭ]

Yliopisto

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ