የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 5/15 ገጽ 32
  • ለግንባታ ፕሮግራም ያነሳሳ ቃጠሎ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለግንባታ ፕሮግራም ያነሳሳ ቃጠሎ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 5/15 ገጽ 32

ለግንባታ ፕሮግራም ያነሳሳ ቃጠሎ

“ቃጠሎ! ቃጠሎ! የይሖዋ ምሥክሮች የስብሰባ አዳራሽ ተቃጠለ!” ይህ አስደንጋጭ ጩኸት የተሰማው አርብ ከሰዓት በኋላ በጥቅምት ወር 1989 በኔዘርላንድስ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው በሄርንቬን ከተማ ነበር።

የይሖዋ ምሥክሮች ይህን ውብ የሆነ ትልቅ የስብሰባ አዳራሽ ለ11 ዓመታት ተገልግለውበታል። ሁልጊዜ ቅዳሜና እሁድ ለማለት ይቻላል፣ በመቶ የሚቆጠሩ ተሰብሳቢዎች በዚህ አዳራሽ ተገኝተው ለአንድ ቀን የሚደረገውን የልዩ ስብሰባ ወይም ለሁለት ቀን የሚደረገውን የክልል ስብሰባ ፕሮግራም ይከታተሉ ነበር። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የሚሰጥበት አመቺ ሥፍራ ሆኖ ነበር።

በጣሪያው ላይ የጥገና ሥራ በሚከናወንበት ጊዜ በተፈጠረ አደጋ ምክንያት በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ አዳራሹ የፍርስራሽ ክምር ሆነ። ሆኖም የተጐዳ ሰው ባለመኖሩ ይሖዋን አመሰገንን።

ምሥክሮቹ በደረሰው ጥፋት ቢያዝኑም ተስፋ ሳይቆርጡ በሌላ ቦታ አዲስ አዳራሽ ለመሥራት እቅድ አወጡ። በፍለቮላንድ አውራጃ በስዊፍተርባንት ተስማሚ ቦታ አገኙ። ይህም በቀድሞው ዙይደርዚ፣ ከባሕር ወለል 16 ጫማ ዝቅ ብሎ የሚገኝ ሰፊ ቦታ ነው። ጥር 1991 የአዲሱ ትልቅ የስብሰባ አዳራሽ ሥራ እንደሚጀመር ማስታወቂያ ተነገረ። ከግንቦት እስከ መስከረም 1991 ባለው ጊዜ ውስጥ ተሠርቶ ማለቅ ነበረበት። በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ምሥክሮች በግንባታው ሥራ ለመሳተፍ በፈቃደኝነት መጡ። ይህ ፕሮጀክት ለአንዳንድ ወጣት ወንዶች ይሖዋ አምላክን በሙሉ ጊዜ ወደማገልገል የሚያሸጋግራቸው ድልድይ ሆኖ አግኝተውታል። ከቤልጅየም እና ከኢንግላንድ የመጡ ብዙ ሠራተኞች ነበሩ።

በጣም ውብ የሆነ ሕንፃ ተሠራ። የመሰብሰቢያው አዳራሹ ከመስታወት የተሠራ ጣሪያ ባለው መተላለፊያ ከመመገቢያ ክፍሎች ተለይቶአል። ዋናው አዳራሽ 1,008 ሰዎችን የሚይዝ ወንበሮች አሉት። እንዲሁም ፕሮግራሙን በቴሌቪዥን ለመከታተል የሚያስችል 230 ሰዎችን የሚያስቀምጥ ሌላ አዳራሽ አለ።

ዛሬ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች “ኑ፣ ወደ ይሖዋ ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፣ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል” እያሉ ነው። (ኢሳይያስ 2:2, 3) ይህ አዲስ የስብሰባ ትልቅ አዳራሽ እንደዚህ ያለው መንፈሳዊ ትምህርት ከሚሰጥባቸው ቦታዎች አንዱ ነው። በየአካባቢው የሚገኙት የይሖዋ ምሥክሮች የመንግስት አዳራሾችም ይህ ዓይነቱ ትምህርት የሚሰጥባቸው ቦታዎች ናቸው። እዚያም ሞቅ ያለ አቀባበል ይደረግላችኋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ