የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 9/15 ገጽ 32
  • የአምላክን ስም ያውቁ ነበር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአምላክን ስም ያውቁ ነበር
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 9/15 ገጽ 32

የአምላክን ስም ያውቁ ነበር

በእንግሊዝ የአሜሪካ ቅኝ ግዛቶች ውስጥ ለመጻፍና ለመሰራጨት የመጀመሪያ የሆነው የሥነ ጽሑፍ ጥንቅር የቤይ የመዝሙር መጽሐፍ ነው። የመጀመሪያው እትም በ1640 በማሳቹሴትስ ቤይ ኮሎኒ ውስጥ በስቴፈን ዳይ ታተመ። መጽሐፉ ከዕብራይስጥ በዚያን ጊዜ ይነገርና ይጻፍ ወደነበረው እንግሊዝኛ ቋንቋ የተተረጎመ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሆነውን የመዝሙር መጽሐፍ የያዘ ነበር።

የቤይ የመዝሙር መጽሐፍ አስደናቂ ገጽታው በአንዳንድ ቁጥሮች ላይ መለኮታዊውን ስም መጠቀሙ ነበር። ስለዚህ ከ350 ያህል ዓመታት በፊት ያንን ጽሑፍ ያነብ የነበረ ማንኛውም ሰው የፈጣሪን ስም ሊያውቅ ይችል ነበር። ለምሳሌ ያህል በዚያ እትም ላይ መዝሙር 83:17, 18 “ይገረሙ፣ ይታወኩም። አዎ፣ ይፈሩ፣ ይጥፉም። ሰዎች ስምህ ይሖዋ የሆንከው አንተ ብቻ በምድር ሁሉ ላይ ከፍ ያልክ ልዑል እንደሆንህ ይወቁ” ይላል።

በእርግጥ ልዑሉ አምላክ ስሙ ይሖዋ መሆኑን አምነን ከመቀበል የበለጠ ነገር ይፈለግብናል። በቤይ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝሙር መጽሐፍ ላይ መዝሙር 1:1, 2 “የተባረከ ሰው” በክፉዎች ምክር እንደማይሄድ፣ “ነገር ግን በአምላኩ በይሖዋ ሕግ ደስ እንደሚለው” ይናገራል። እንደገና ታርሞ በታተመው ኒው ኢንግላንድ ትርጉም ላይ ሠፍሮ እንደሚገኘው የ1648ቱ የመዝሙር ትርጉም “መላ ደስታውን በይሖዋ ሕግ ላይ ያደርጋል” ይላል።

እዚህ ላይ የ20ኛው መቶ ዘመን የቅዱሳን ጽሑፎች የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም “በክፉዎች ምክር ያልሄደ፣ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፣ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ ሰው ደስተኛ ነው። ደስታው ግን በይሖዋ ሕግ ነው፣ ሕጉንም ድምፅ ሳያሰማ በቀንና በሌሊት ያነባል” ይላል።

አንድ ሰው በእርግጥ ደስተኛ እንዲሆን ከፈለገ የክፉዎችን ምክር መናቅ አለበት። የኃጢአተኞችን ምሳሌነት መከተልና ከአምላክ የለሽ ዋዘኞች ወይም ቀልደኞች ጋር መተባበር የለበትም። ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ በምክራቸውና በተግባራቸው ወደ ፆታ ብልግና፣ የዕፅ ሱሰኝነትና ከአምላክ ሕግ ጋር ወደሚቃረኑ ሌሎች ተግባሮች ስበው ከሚያስገቡ ሰዎች ጋር አብሮ መሆንን ማስወገድ ያስፈልገዋል። አዎ፣ እውነተኛ ደስታ የተመካው ስሙ ይሖዋ ስለሆነው እውነተኛ አምላክ በማወቅና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጸውን ሕጉን በሥራ ላይ በማዋል ላይ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ