የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 12/1 ገጽ 32
  • “እንደሚያገሣ አንበሳ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “እንደሚያገሣ አንበሳ”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 12/1 ገጽ 32

“እንደሚያገሣ አንበሳ”

በሰይጣን መኖር ታምናለህን? በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች ሰይጣን መኖሩን አያምኑም። እንዲህ ዓይነቱን እምነት የሚመለከቱት “ኢሳይንሳዊ” እንደሆነ አድርገው ነው። ገና በ1911 እንኳን ኢንሳይክሎፔድያ ብሪታኒካ “ሳይንስ አብዛኛውን የሰው ውጪያዊ የባሕሪ ሂደትና ውስጣዊ ሕይወት በሚገባ የገለጸው ስለሆነ ሰይጣናዊ ግፊት አለ ብሎ ለማመን ምንም ቦታ የለም” ብሎ ነበር። የሃይማኖት ሊቃውንት ሰይጣን ምሳሌ ወይም ተረት ብቻ ነው ብለው ያስባሉ። ዘ ወርልድ ቡክ ኢንሳይክሎፔድያ “ብዙ ዘመናውያን የሃይማኖት ሊቃውንት ዲያብሎስ የክፋት ኃይል፣ የመጨረሻው ክፉ የሆነ የሰው ባሕሪ ምሳሌ እንደሆነ ይቆጥራሉ” በማለት ተናግሮ ነበር።

ይሁንና ሐቁ ምንድን ነው? በመጽሐፍ ቅዱስ የምታምን ከሆነ ሰይጣን እውን እንደሆነ ማመን ይኖርብሃል። ኢየሱስ ሰይጣን መኖሩን ማመን ብቻ ሳይሆን “የዚህ ዓለም ገዢ” በማለት ጠርቶታል። (ዮሐንስ 14:30) ሐዋርያው ጳውሎስ ሰይጣንን “የዚህ ዓለም አምላክ” ብሎ ጠርቶታል። (2 ቆሮንቶስ 4:4) አረጋዊው ሐዋርያ ዮሐንስም “ዓለምም በሞላው በክፉው ተይዟል” ብሏል።—1 ዮሐንስ 5:19

ከዮሐንስ ጋር የማትስማማ ከሆነ በቅርብ ጊዜ ስለተፈጸመው ታሪክ አስብ። ስለ ረብሻ ቡድኖችና በመንግሥታት ስለሚፈጸመው ሰዎችን በድብደባ ማሰቃየት አስብ። የእኛ ትውልድ ያያቸውን ጦርነቶችና በዘር፣ በሃይማኖት ወይም በፖለቲካ ልዩነት ላይ የተመሠረቱ እልቂቶች አስታውስ። በጋዜጦቻችን ላይ ከሚሠፍሩት አሰቃቂ ወንጀሎች ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል ብዛት ስላላቸው ነፍስ ግድያዎች፣ አስገድዶ በጾታ ስለመድፈር፣ ሰዎችን በጅምላ ስለመጨፍጨፍ፣ ልጆችን ያለ አገባብ ለጾታ መጠቀሚያ ስለማድረግ ምን ለማለት ይቻላል? የዚህ ዓለም አምላክ ከሰይጣን ሌላ ሊሆን ይችላልን?

ሐዋርያው ጴጥሮስ “ንቁ፣ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና” በማለት አስጠንቅቋል። (1 ጴጥሮስ 5:8) አንድ አንበሳ በአቅራቢያህ ተፈትቶ ቢለቀቅ አንበሳው አለ የለም እያልክ ስለ ሕልውናው እያወራህ ትዘገይ ነበርን? ወይስ ለማምለጥ ትሮጥ ነበር?

ሰይጣን ስለመኖሩ እርግጠኛ ሁን። ምሕረት የለሽና ጨካኝ ነው፤ ከእኛም የበለጠ ኃይለኛ ነው። ስለዚህ መሸሸጊያ ለማግኘት ከእርሱም የበለጠ ኃያል ወደሆነው ሮጠህ ተጠጋ። “የእግዚአብሔር [የይሖዋ አዓት] ስም የጸና ግንብ ነው፤ ጻድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል [መጠጊያ ያገኛል አዓት]።” (ምሳሌ 18:10) መጠለያህን ከይሖዋ አምላክ ዘንድ አድርግ፤ በቅርቡም የሰው ዘር ከክፉው ሰይጣን ተጽእኖዎች የሚላቀቅ መሆኑንም እወቅ። ይህስ ምንኛ የሚያስደስት እፎይታ ይሆን!—ራእይ 20:1-3

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ