የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 1/15 ገጽ 31
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ነጠላነትንና ትዳርን አስመልክቶ የተሰጠ ጥበብ ያዘለ ምክር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ነጠላነታችሁን በጥበብ ተጠቀሙበት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • የነጠላነት ኑሮ የኢኮኖሚ ችግር ባለበት ጊዜ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • በይሖዋ አገልግሎት ደስተኛ የሆኑ ያላገቡ ክርስቲያኖች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
ለተጨማሪ መረጃ
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 1/15 ገጽ 31

የአንባብያን ጥያቄዎች

አንድ ክርስቲያን ወይም አንዲት ክርስቲያን ተስማሚ የትዳር ጓደኛ ማግኘት ባይችል ወይም ባትችል ምን ማድረግ ይኖርባቸዋል?

ምንም እንኳን ለአምላክ ያደርን ክርስቲያኖች ብንሆንም ይፈጸማል ብለን አጥብቀን ተስፋ ያደረግነው አንድ ነገር ሳይፈጸም ሲቀር እናዝናለን። ይህ ዓይነቱ ስሜታችን “የምትዘገይ ተስፋ ልብን ታሳዝናለች” ሲል በሚናገረው በምሳሌ 13:​12 ላይ በሚገባ ተገልጿል። አንዳንድ ክርስቲያኖች ለማግባት ፈልገው የሚስማማቸውን የትዳር ጓደኛ ለማግኘት ሳይችሉ ሲቀሩ የተሰማቸው ልክ እንደዚህ ነው። በተለይ ሐዋርያው ጳውሎስ ‘በሥጋ እንደሚቃጠሉ’ የተናገረላቸው ሰዎች ይህ ዓይነቱ ስሜት ያስቸግራቸዋል። — 1 ቆሮንቶስ 7:9

የጎደለንን ነገር ከተቃራኒ ጾታ በማግኘት እውነተኛ ሙሉነት ለማግኘት መፈለግን ይሖዋ በሰው ልጆች ልብ ውስጥ አስቀምጧል። ስለዚህ አንዳንድ ነጠላ ክርስቲያኖች እንዲህ ያለው ጠንካራ ስሜት ቢያድርባቸው የሚያስደንቅ አይሆንም። (ዘፍጥረት 2:​18) ያላገቡ ክርስቲያኖች ጋብቻን (ወይም በተወሰነ ዕድሜ ላይ ማግባትን) በሚያጠብቅ ባሕል ሥር ሲሆኑ ወይም በጉባኤያቸው ውስጥ በሚገኙ ደስተኛ ባለ ትዳሮች በሚከበቡበት ጊዜ ይህ ዓይነቱ ስሜት ሊባባስባቸው ይችላል። ይሁን እንጂ እንዲህ ያለውን ጉጉት ረዘም ላለ ጊዜ እንዲቆይ መፍቀድ ጥሩ አይደለም። ታዲያ ቅን የሆኑ ክርስቲያኖች እንዲህ ባለው ሁኔታ ከሚገባው በላይ ሳይረበሹ ሊቋቋሙት የሚችሉት እንዴት ነው?

እንዲህ ያለውን ሁኔታ መቋቋም ቀላል አይደለም፤ ሌሎችም ቢሆኑ ይህንን ጭንቀታቸውን ችግሮችን እንደማጋነን ወይም እንደ ቅብጠት አድርገው መመልከት የለባቸውም። ነገር ግን ይህን ዓይነቱን ሁኔታ መቋቋም ወይም ለነገሩ መፍትሔ ማስገኘት ያላገባው ሰው ሊወስዳቸው በሚችላቸው እርምጃዎች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የተመካ ነው።

“ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ [ይበልጥ ደስተኛ አዓት] ነው” በሚለው ተግባራዊ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓት ውስጥ ቁልፍ የሆነ አንድ ሐሳብ እናገኛለን። (ሥራ 20:​35) ይህ የተነገረው ነጠላ በነበረው በኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህንንም ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ በሚገባ ያውቅ ነበር። ከራስ ወዳድነት በራቀ ስሜት ተገፋፍተን ለሌሎች አንዳንድ ነገሮችን ማድረግ በዘገየ ተስፋ የሚመጣውን ስሜት ለመቋቋም የሚረዳ ጥሩ መድኃኒት ነው። በነጠላው ክርስቲያን በኩል ሆነን ስንመለከተው ይህ ምን ማለት ነው?

ለራሳችሁ ቤተሰብ አባሎችና ለክርስቲያን ጉባኤ አባሎች የደግነት ሥራ ለመሥራት እንዲሁም በሁሉም የመንግሥቱ አገልግሎት ዘርፎች ያላችሁን እንቅስቃሴ ለማሳደግ ጣሩ። ይህ ምክር ‘በሥራ ስትጠመድ ለማግባት ያለህን ፍላጎት ትረሳዋለህ’ እንደሚባለው ዓይነት አነጋገር አይደለም። ውጤት ባላቸው በእነዚህ ክርስቲያናዊ ተግባሮች ስትጠመዱ ‘ሳትናወጡ ልባችሁ በአንድ አቋም ሊጸናና በራሳችሁ ፈቃድ ላይ ሥልጣን ሊኖራችሁ’ ይችላል፤ እንዲሁም በአሁኑ ጊዜ የምትገኙበትን ሁኔታ ጠቃሚ በሆነ መንገድ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ። — 1 ቆሮንቶስ 7:⁠37

ለማግባት በጣም የሚፈልጉ አንዳንዶች ይህ ፍላጎታቸው ጊዜያቸውን የሚያጠፋ አስጨናቂ ሐሳብ እንዲሆንባቸው ፈቅደዋል። እንዲያውም የትዳር ጓደኛ እንደሚፈልጉ በመግለጽ በጋዜጦች ላይ ማስታወቂያ እስከማውጣት ድረስ ደርሰዋል። በነጠላነት ጊዜ ሊገኝ የሚችለውን ጥቅም ይበልጥ ማድነቅ ግን እንዴት የተሻለ ነው! — በመጠበቂያ ግንብ 11–108 ላይ የወጣውን “ሳያገቡ ለአምላክ አገልግሎት ሙሉ መሆን” የሚለውንና “ነጠላነት መልሶ የሚክስ የሕይወት መንገድ ነው” የሚለውን እንዲሁም ግንቦት 15, 1992 የወጣውን “ጋብቻ ደስታ የሚገኝበት ብቸኛ ቁልፍ ነውን?” የሚለውን ርዕሰ ትምህርት ተመልከቱ።

ይሖዋ በነጠላነት ለመቆየት ትችሉ ዘንድ እንዲረዳችሁ ጸልዩ። (ፊልጵስዩስ 4:​6, 7, 13) ያላገቡ ብዙ ክርስቲያኖች ያላቸውን ትርፍ ጊዜ የአምላክን ቃል ለማጥናትና በእርሱም ላይ ለማሰላሰል እንዲሁም በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ለመገኘትና ለመካፈል ስለተጠቀሙበት ኢየሱስ እርሱን ለሚከተሉት ሰዎች እንደሚሰጣቸው ቃል የገባውን ተጨማሪ ‘የመንፈስ እረፍት’ በማግኘት ተደስተዋል። (ማቴዎስ 11:​28–30) ይህም ከጊዜ በኋላ ተስማሚ የትዳር ጓደኛ ካገኙ የተሻሉ ባሎች ወይም የተሻሉ ሚስቶች እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን መንፈሳዊነት እንዲያዳብሩ ረድቷቸዋል።

ይሖዋ እርሱን የሚያገለግሉትን ነጠላ ሰዎች ሁኔታ እንደሚረዳ ፈጽማችሁ አትርሱ። አሁን ያላችሁበት ሁኔታ እናንተ የምትመርጡት ዓይነት ላይሆን እንደሚችል ያውቃል። አፍቃሪው የሰማይ አባታችን በመንፈሳዊም ሆነ በስሜታዊ ሁኔታ ለዘለቄታው የሚጠቅመንን ነገር ያውቃል። እናንተም ይሖዋን በትዕግሥት ከተጠባበቃችሁና የቃሉን መሠረታዊ ሥርዓቶች በዕለታዊ ኑሮአችሁ ተግባራዊ ካደረጋችሁ ይበልጥ የሚያስፈልጓችሁን ነገሮች ዘላለማዊ ጠቀሜታ በሚያስገኝ መንገድ እንደሚያሟላላችሁ እርግጠኞች ልትሆኑ ትችላላችሁ። — ከመዝሙር 145:​16 ጋር አወዳድር

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ