የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 5/15 ገጽ 30
  • የትዕቢተኝነትን መንፈስ አስወግድ!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የትዕቢተኝነትን መንፈስ አስወግድ!
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 5/15 ገጽ 30

የትዕቢተኝነትን መንፈስ አስወግድ!

አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌ እንዲህ ይላል:- “ ደጁንም ዘለግ የሚያደርግ ውድቀትን ይሻል።” (ምሳሌ 17:​19 ) የአጥር ግቢ በሩ ከፍ ከፍ ተደርጎ መሠራቱ ስህተቱ ምን ላይ ነው? የምሳሌው ፍሬ ነገር ምንድን ነው?

በጥንት ዘመን በተናጠልም ሆነ በቡድን በፈረስ ላይ ተቀምጠው የሚዘርፉ ወንበዴዎች ያልተለመዱ አልነበሩም። ገላጣ በሆነ የገጠር መንደር ውስጥ አጥር ያልነበራቸው ቤቶች ለሌቦች የተጋለጡ ነበሩ። አንዳንድ የቤት ባለቤቶች ንብረቶቻቸውን ከስርቆት ለመከላከል ልዩ የመግቢያ በር ያለው አጥር ይገነቡ ነበር። አጥሩ ከፍ ያለ ሲሆን መግቢያው በር ግን አጭር ነበር። አንዳንዶቹ እንዲያውም ከአንድ ሜትር ከፍታ በላይ ስላልነበራቸው ፈረሱንና ፈረሰኛውን በአንድ ላይ ሊያስገቡ አይችሉም ነበር። ወደ ግቢያቸው የሚያስገባውን በር ዝቅ አድርገው ያላሠሩ በፈረስ ላይ ተቀምጠው ንብረቶችን ለሚዘርፉ ሰዎች ይጋለጣሉ።

በከተማ ውስጥ የሚገኙ የአጥር ግቢ በሮች ዝቅ ያሉና ለዓይን የማይማርኩ ነበሩ። በታጠረው ግቢ ውስጥ ሊኖረው ስለሚችለው ሀብት ምንም ዓይነት ፍንጭ አይሰጡም ነበር። ይሁን እንጂ በፋርስ ውስጥ ትልቅና ማራኪ በር የንጉሣውያን ቤተሰብ አንዱ ምልክት ስለነበር አንዳንድ ሰዎች እነሱን ለመምሰል በመሞከር ራሳቸውን አደጋ ላይ ይጥሉ ነበር። የግቢውን አጥር በር ከፍ አድርጎ የሠራ ማንኛውም ሰው ብልጽግናውን ስለሚያሳይ ዘረፋን ይጋብዝ ነበር።

ስለዚህ ከዚህ መረዳት እንደምንችለው ምሳሌ 17:19 ራሳቸውን ከፍ ከፍ በማድረግ የግቢያቸውን በር የሚያስረዝሙ ሰዎች በራሳቸው ላይ መከራን እንደሚጠሩ ያሳያል። ይህ ምሳሌ ጉራ ሲነዛና በዕብሪት ሲነገር በጣም የሚከፈተውን አፍ ከፍ ተደርጎ ከተሠራው በር ጋር የሚያወዳድር ሊሆን ይችላል። ይህ ዓይነቱ አነጋገር ጥልን በማነሳሳት የኋላ ኋላ ኩራተኛውን ሰው ወደ ጥፋት ሊመራው ይችላል። እንግዲያው የትዕቢተኝነትን መንፈስ ማስወገድ ምንኛ ጥበብ ነው!

[ምንጭ]

Picturesque Palestine, Sinai and Egypt, Volume 1, by Colonel Wilson (1981)

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ