የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 6/15 ገጽ 31
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ቁማርን ያወግዛል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ቁማር
    ንቁ!—2015
  • በቁማር ወጥመድ ላለመያዝ መጠንቀቅ
    ንቁ!—2002
  • የመጽሐፍ ቅዱስ አመለካከት
    ንቁ!—1995
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 6/15 ገጽ 31

የአንባብያን ጥያቄዎች

ክርስቲያኖች በገንዘብ ቁማር አይጫወቱም። ይሁን እንጂ ዕጣ የወጣላቸው ሰዎች ምንም ነገር ሳይከፍሉ ገንዘብ ወይም አንድ ዕቃ ሊያገኙ በሚችሉበት ዝግጅት ውስጥ ለመሳተፍ ዕጣ ማውጣት ወይም ቲኬት መቀበል ይችላሉን?

ይህ ጥያቄ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ የተጠየቀ በመሆኑ በጽሑፎቻችን ላይ ቀደም ሲል ተጠቅሷል። በአንዳንድ ቋንቋዎች የጽሑፎቻችን ማውጫ የሚሆኑ ለምሳሌ ከ1930–1985 ለወጡት የመጠበቂያ ግንብ ጽሑፎች ማውጫ (በተመሳሳይም ከ1986–1990 ያሉትን የሚሸፍን) አዘጋጅተናል። አንድ ክርስቲያን በቋንቋው እነዚህ ማውጫዎች ካሉት አጥጋቢ መልሶችን ወዲያው በቀላሉ ለማግኘት የሚችልባቸውን ጽሑፎች ሊጠቁሙት ይች⁠ላሉ።

ከላይ የተጠየቀው ጥያቄ እንደ ምሳሌ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። የ1930–1985 ማውጫ “የአንባብያን ጥያቄዎች” በሚለው አርዕስት ሥር “‘ዕጣዎች’፣ አንድ ክርስቲያን ቲኬት ሊቀበል ይችላልን?” የሚለውን ንዑስ ርዕስ ያገኛል። አንባቢው በየካቲት 15, 1973 መጠበቂያ ግንብ እትም ገጽ 127 ላይ የወጣውን “የአንባብያን ጥያቄዎች” የሚለውን ክፍል እንዲያነብ ተጠቅሶለታል።a ብዙ ምስክሮች የ1973 መጠበቂያ ግንብ ጥራዝ (ወይም ነጠላ መጽሔቶች) አላቸው፤ አለበለዚያም በመንግሥት አዳራሾች ውስጥ በሚገኘው ቤተ መጻሕፍት ሄደው ማየት ይችላሉ።

በ1973 በታተመው ጽሑፍ ላይ ክርስቲያኖች ሁሉ ማንኛውንም ዓይነት ውርርድ፣ በቲኬት ዕድልን መግዛት አስፈላጊ የሚሆንባቸውን ዕጣዎች ወይም ሎተሪዎች ያስወግዳሉ ወይም በዕጣ የሚገኝ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ገንዘባቸውን አያወጡም ይላል። በቀላል አነጋገር፣ የስግብግብነት መግለጫ የሆነውን ቁማር አንጫወትም። — 1 ቆሮንቶስ 5:​11፤ 6:​10፤ ኤፌሶን 4:​19፤ 5:​3, 5

ይሁን እንጂ አንድ ሱቅ ወይም የንግድ ድርጅት ሸቀጡን ለማስተዋወቅ ሲል በዕጣ አማካኝነት ሽልማት ሊሰጥ ይፈልግ ይሆናል። በዕጣው የሚካፈለው ሰው በገንዘብ ምንም ነገር ሳይገዛ ስሙን ወይም እንደ ቲኬት ዓይነት ነገር ብቻ ይልክ ይሆናል። ዕጣው ሸቀጡን ማስተዋወቂያ መሣሪያ ብቻ ሆኖ የሚያገለግልና አድልዎ በሌለበት ሁኔታ ሽልማቱን ወይም ሽልማቶቹን ለመስጠት የሚያስችል መሣሪያ ብቻ ነው። አንዳንድ ክርስቲያኖች እንዲህ ዓይነቱ ዕጣ ቁማር እንዳልሆነ በማሰብ ሽልማቱን ሊቀበሉ እንደሚችሉ ይሰማቸው ይሆናል። አንድ ሱቅ ወይም የንግድ ድርጅት የማስተዋወቂያ ፕሮግራሙ ክፍል አድርጎ አንዳንድ ስጦታዎችን ወይም ነፃ ናሙናዎችን ሲሰጥ ሊቀበሉ እንደሚችሉት አድርገው ያዩታል ማለት ነው።

ይሁን እንጂ አንዳንድ ክርስቲያኖች ሌሎችን ላለማደናቀፍ ወይም ግራ ላለማጋባት ወይም ‘በዕድል አምላክ’ ላይ ምንም ዓይነት እምነት የሌላቸው መሆኑን ለማሳየት ሲሉ እንዲህ ካለው ተግባር ሙሉ በሙሉ ይርቃሉ። ኢሳይያስ 65:​11 እንደሚያመለክተው የአምላክ አገልጋዮች ዕድል ከተባለው አምላክ ጋር ምንም ዓይነት ተካፋይነት እንዲኖራቸው አይፈልጉም። የዕጣው አሸናፊዎች ለሕዝብ እንዲታዩ በሚደረጉ ዝግጅቶችም ለመካፈል አይፈልጉ ይሆናል። እንዲህ የሚሰማቸው ክርስቲያኖች ሁሉ ከላይ በተገለጸው ዓይነት ዕጣ ሊካፈሉ እንደሚችሉ የሚሰማቸውን ክርስቲያኖች መተቸት ወይም መንቀፍ አይገባቸውም። — ከሮሜ 14:​1–4 ጋር አወዳድር።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ይኸው ትምህርት “ማስታወቂያ”፣ “ንግድ” እና “ቁማር” በሚሉት ርዕሶች ሥር ተጠቅሶ ስለሚገኝ የማውጫው የተለያየ አቀራረብ አንድን ሰው ስለጉዳዩ የተብራራውን ትምህርት በቀላሉ የሚያገኝባቸውን ጽሑፎች ሊጠቁመው ይችላል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ