የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 8/15 ገጽ 31
  • ታስታውሳለህን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታስታውሳለህን?
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ ከአብርሃም ጋር ቃል ኪዳን ገባ
    መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
  • ይሖዋ “ወዳጄ” በማለት ጠርቶታል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • አብርሃም—አፍቃሪ ሰው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • “ልባችሁን አጽኑ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
ለተጨማሪ መረጃ
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 8/15 ገጽ 31

ታስታውሳለህን?

በቅርቡ የወጡት የመጠበቂያ ግንብ መጽሔቶች ተግባራዊ ጠቀሜታ ያላቸው ሆነው አግኝተሃቸዋልን? ታዲያ በሚከተሉት ጥያቄዎች አማካኝነት ችሎታህን ለምን አትፈትንም?

▫ ሳንፈልገው ማንኛውም ከሥነ ምግባር ውጭ የሆነ ሐሳብ ወደ አእምሮአችን ቢመጣ ምን ማድረግ ይኖርብናል?

የምናስበውን ነገር መለወጥ። ወጣ ብለን በእግር መሄድ፣ ማንበብ ወይም የቤት ውስጥ ሥራ መሥራት ይኖርብናል። በዚህ ረገድ ጸሎት ከፍተኛ እርዳታ ያበረክታል። (መዝሙር 62:​8) 4/15 ገጽ 17

▫ ወጣቶች የሚሰሙትን የሙዚቃ ዓይነት በተመለከተ መጠንቀቅ ያለባቸው ለምንድን ነው?

ሙዚቃ የመቀስቀስ፣ የማነሳሳትና የመገፋፋት ኃይል አለው። ብዙዎቹ ሙዚቃዎች የሥነ ምግባር ርኩሰትን በተዘዋዋሪ ሁኔታ የሚያሞግሱና ወደ ብልግና የሚያመሩ ስለሆኑ የዘፈን ቅጂዎችን፣ ካሴቶችንና ሸክላዎችን በመምረጥ ረገድ ከባድ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ ግልጽ ነው። — 4/15 ገጽ 20–1

▫ ‘የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መገኘት’ የሚለው አገላለጽ ምን ማለት ነው? (1 ተሰሎንቄ 5:​23)

ይህ አገላለጽ የሚያመለክተው ኢየሱስ በሰማይ መንገሥ ከጀመረበት ከ1914 ጀምሮ ያለውን በዓይን የማይታየውን የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ንጉሣዊ መገኘት ነው። (መዝሙር 110:​1, 2) — 5/1 ገጽ 11

▫ ይሖዋ መንፈሳዊ ቤተ መቅደሱን ማጽዳቱ ምን ዓላማ አከናውኗል? (ሚልክያስ 3:​1–4)

ምድራዊ ተስፋ ያላቸው በጣም ብዙ አምላኪዎች ወደፊት ሲመጡ ጽንፈ ዓለማዊ ሉዓላዊነቱ የሚከበርበት፣ መለኮታዊ ስሙ የሚቀደስበትና የጽድቅ ሕግጋቱ የሚከበሩበት ቦታ ተዘጋጅቶላቸው እንዲቆይ ይሖዋ ቤተ መቅደሱ ንጹሕ በሆነ ሁኔታ እንዲገኝ ፈልጎ ነበር። — 5/1 ገጽ 16

▫ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሾማቸው ባሪያዎቹ የሰጣቸው “ባለው ሁሉ ላይ” የተባሉት ንብረቶቹ ምንድን ናቸው? (ማቴዎስ 24:​45–47)

ክርስቶስ ሰማያዊ ንጉሥ በመሆን ካገኘው ሥልጣን ጋር የተያያዙትን መንፈሳዊ ንብረቶች ሁሉ ያመለክታሉ። ይህም ከአሕዛብ ሁሉ ለክርስቶስ ደቀ መዛሙርት የማድረግን ተልዕኮ ይጨምራል። (ማቴዎስ 28:​19, 20) — 5/1 ገጽ 17

▫ ጴጥሮስ በ1 ጴጥሮስ 5:​2 ላይ አጥብቆ ባሳሰበው መሠረት ክርስቲያን ሽማግሌዎች በእረኝነታቸው ‘ውዴታ’ የሚያሳዩት እንዴት ነው?

ለበጎቹ የሚጨነቅ አንድ ክርስቲያን የበላይ ተመልካች እንዲህ የሚያደርገው በፈቃደኝነት፣ በራሱ ነፃ ፈቃድ፣ በመልካሙ እረኛ በኢየሱስ ክርስቶስ መመሪያ ሥር በመሆን ነው። ከዚህም በተጨማሪ “በውዴታ” ማገልገል ማለት አንድ ክርስቲያን እረኛ ‘የነፍሳችን እረኛና የበላይ ተመልካች’ ለሆነው ለይሖዋ ሥልጣን ይገዛል ማለት ነው። — 5/15 ገጽ 20

▫ ኢየሱስ እሱን የሚከተል ሁሉ “ራሱን መካድ” አለበት ሲል ምን ማለቱ ነበር? (ማቴዎስ 16:​24)

‘ራስን መካድ’ ማለት በራስህ ላይ ያለህን የባለቤትነት መብት ለይሖዋ ታስረክባለህ ማለት ነው። (1 ቆሮንቶስ 6:​19, 20) ይህም ማለት የምትኖረው ራስህን ለማስደሰት ሳይሆን አምላክን ለማስደሰት ነው። (ሮሜ 14:8) — 6/1 ገጽ 9

▫ አንድ ሰው ደስተኛ እንዲሆን የሚያስፈልገው ምንድን ነው?

ከይሖዋ ጋር አስደሳች ዝምድና መመሥረትና በይሖዋ አገልግሎት ሥራ የበዛለት ሆኖ መቀጠል በግለሰቡ ሕይወት ውስጥ እውነተኛ ደስታ ያመጣለታል። — 6/1 ገጽ 22

▫ ሰዶምን ለማጥፋት ስላለው ዓላማ አብርሃም በነፃነት እንዲያነጋግረው ይሖዋ የፈቀደለት ለምንድን ነው? (ዘፍጥረት 18:​22–32)

አንዱ ምክንያት አብርሃም የአምላክ ወዳጅ ነበር። (ያዕቆብ 2:​23) በተጨማሪም አብርሃም ያደረበትን የጭንቀት ስሜት ይሖዋ ስለተገነዘበ ነው። የአብርሃም የወንድም ልጅ የሆነው ሎጥ በሰዶም ይኖር ስለነበር አብርሃምን ያሳሰበው ጉዳይ የሎጥ መትረፍ እንደሆነ ይሖዋ አውቋል። በእነዚህ ምክንያቶች የተነሳ ይሖዋ ሰዶምን ለማጥፋት ስለነበረው ዓላማ ለአብርሃም ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ሆኗል። — 6/15 ገጽ 16

▫ የ16ኛው መቶ ዘመን የፕሮቴስታንት ሃይማኖታዊ ተሐድሶ እውነተኛውን ክርስትና መልሶ አመጣውን?

አላመጣውም። የተሐድሶ ለውጡ እውነተኛውን ክርስትና መልሶ ከማቋቋም ይልቅ ለፖለቲካዊ መንግሥታት የሚያጎበድዱና ጦርነቶቻቸውን የሚደግፉ በርካታ ብሔራዊና ክልላዊ አብያተ ክርስቲያናት እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኖአል። — 7/1 ገጽ 10–11

▫ ኢየሱስ በማቴዎስ 6:​20 ላይ የተናገረለት ‘በሰማይ የሚገኝ መዝገብ’ ምንድን ነው?

ይህ መዝገብ ለመቼውም የማይጠፋ ሲሆን በይሖዋ ዘንድ ጥሩ ስም ማግኘትንና የታመነ የክርስቲያናዊ አገልግሎት መዝገብን ይጨምራል። እነዚህም ይሖዋ በፍጹም ከማይረሳቸው ነገሮች መካከል ናቸው። (ዕብራውያን 6:​10) — 7/1 ገጽ 32

▫ ጴጥሮስ ለእምነታችን በጣም አስፈላጊ እንደሆኑ አድርጎ የጠቀሳቸው ባሕሪያት ምንድን ናቸው? (2 ጴጥሮስ 1:​5–7)

ጴጥሮስ በጎነት፣ እውቀት፣ ራስን መግዛት፣ ጽናት፣ ለአምላክ ያደሩ መሆን፣ የጠበቀ ወንድማዊ መዋደድና ፍቅር በእምነታችን ላይ መጨመር የሚኖርባቸው ነገሮች ናቸው በማለት ገልጿል። — 7/15 ገጽ 13

▫ ዳዊት ከቤርሳቤህ ጋር ስለ ሠራው ኃጢአት የሚናገረው ታሪክ ለአምላክ አገልጋዮች ምን ማስጠንቀቂያ ይዟል? (2 ሳሙኤል 11:​2–4)

በራሱ ጋብቻ በጾታ ለመደሰት ነፃነት ቢኖረውም ዳዊት ሕገወጥ የሆነ የጾታ ምኞት በውስጡ እንዲያድግ ፈቀደ። የኦርዮን ሚስት ምን ያህል ውብ እንደሆነች ተመለከተና ከእርሷ ጋር ሕገወጥ በሆነ መንገድ የመደሰቱን ሐሳብና ድርጊት አልገታውም። ከእንዲህ ዓይነቱ ስግብግብነት ካልሸሸ በማንኛውም የአምላክ አገልጋይ ላይ ተመሳሳይ ሁኔታ ሊከሰት ይችላል። (ያዕቆብ 1:​14, 15) — 8/1 ገጽ 14

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ