የምትሄደው ወደ ሰማይ ነው ወይስ ወደ ሲኦል?
“ወደ ሰማይ ወይም ወደ ሲኦል ለመሄድ ያለህ ዕድል ምን ያህል ነው?”
ይህ ጥያቄ በቅርቡ በተወሰኑ አሜሪካውያን ላይ በተካሄደ ጥናት ላይ የቀረበ ነበር። የፕሪንስተን የሃይማኖት ምርምር ማዕከል የጥናቱን ውጤት ሪሊጅን ኢን አሜሪካ 1992–1993 በተባለው መጽሐፍ ላይ አውጥቷል።
ለጥያቄው ምን መልስ ትሰጣለህ? የትዳር ጓደኛህ ወይም የምታፈቅራቸው ሌሎች ሰዎች በሚሞቱበት ጊዜ ወደ ሰማይ የመሄዳቸው ዕድል ምን ያህል ነው? አንተም ሆንክ እነርሱ በመጨረሻ ወደ ሲኦል ልንወርድ እንችላለን ብለህ ታስባለህን?
78 በመቶ የሚሆኑት ወደ ሰማይ የመሄድ ዕድላችን የሰፋ ነው ብለው እንደሚያስቡ ጥናቱ ያሳያል፤ 40 ከሚያህሉ ዓመታት በፊትም ከዚህ ቁጥር የሚልቁ ሰዎች ይህን መልስ ሰጥተዋል። ስለ ሲኦልስ? 77 በመቶ የሚሆኑት ወደ ሲኦል የመሄድ ዕድላቸው የጠበበ መሆኑን ተናግረዋል።
የሰጧቸው መልሶች በትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት ላይ የተመሰረቱ ናቸውን? ከ10 ሰዎች መካከል 4 የሚሆኑት በሃይማኖታዊ ሥርዓቶች የሚያደርጉት ተሳትፎ ከአምስት ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የቀነሰ መሆኑን አምነዋል። 28 በመቶ የሚሆኑት ብቻ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድኖች እንደሚገኙ፣ 27 በመቶ የሆኑት ብቻ ደግሞ ሃይማኖታዊ ትምህርት እንደሚከታተሉ ተናግረዋል።
መጽሐፍ ቅዱስን በጥንቃቄ ካጠናህ አንዳንድ አስደናቂ የሆኑ እውነታዎችን ታገኛለህ። ለምሳሌ በአንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ላይ አንደተገለጸው መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ሲሞት ወደ “ሲኦል” እንደሄደ በግልጽ ይናገራል። (ሥራ 2:31፤ “ሔድ ስ” የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም ) በተጨማሪም የአምላክ ቃል ንጉሥ ዳዊትም ሆነ መጥምቁ ዮሐንስ ሲሞቱ ወደ ሰማይ እንዳልሄዱ ያረጋግጥልናል። (ማቴዎስ 11:11፤ ሥራ 2:29) እነዚህ ነጥቦች ከሃይማኖታዊ ጥና ት የተገኙ ሐሳቦች ሳይሆኑ የተረጋገጡ እውነታዎች ናቸው።
አንተን ሊነኩ የሚችሉ ሌሎች እውነታዎችም አሉ፦ የኢየሱስ ሐዋርያትና ሌሎች ቁጥራቸው የተወሰነ ሰዎች ከኢየሱስ ጋር ለመግዛት ወደ ሰማይ እንደሚወሰዱ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። ከሞቱ ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ ግን ወደ ሰው ልጆች የጋራ መቃብር ሄደዋ ል። አምላክ ከመቃብር ያስነሣቸዋል። ተመልሳ በምትመጣው ምድራዊ ገነት ውስጥ የተሟላ፣ አስደሳችና ፍጻሜ የሌለው ሕይወት አግኝተው የመኖር ተስፋ ይሰጣቸዋል።
የይሖዋ ምስክሮች ይህ ተስፋ አስተማማኝ መሠረት እንዳለው ከራስህ መጽሐፍ ቅዱስ አውጥተው ሊያሳዩህ ዝግጁ ናቸው።