የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w94 7/15 ገጽ 25
  • የልደት በዓላት ሞት አስከትለዋል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የልደት በዓላት ሞት አስከትለዋል
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
w94 7/15 ገጽ 25

የልደት በዓላት ሞት አስከትለዋል

በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች የልደት በዓል ማክበርን ምንም ጉዳት የሌለው ልማድ አድርገው ይመለከቱታል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ለዚህ ልማድ ጥሩ አይናገርለትም። በመጀመሪያ ደረጃ በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ አንድም ታማኝ የአምላክ አገልጋይ የልደት በዓሉን እንዳከበረ የሚጠቁም ምንም ነገር የለም።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት ሁለት የልደት በዓላት የአምላክ ጠላቶች የነበሩ ሁለት ገዢዎች ያከበሯቸው ናቸው። በሁለቱም በዓላት ላይ አንድ አንድ ሰው እንዲገደል ተደርጓል። ይህም በበዓሉ ላይ የተገኙት እንግዶች ንጉሡን ያስከፋው ሰው በመገደሉ እነሱም እንዲደሰቱ አድርጓቸዋል። ተከበሩ ከተባሉት ልደቶች በመጀመሪያው በዓል ላይ፣ የግብጹ ንጉሥ ፈርዖን የእንጀራ አበዛዎቹን አለቃ አስገድሏል። (ዘፍጥረት 40:2, 3, 20, 22) የግብጹ ገዢ አገልጋዩን በበዓሉ ላይ ያስገደለው ተናዶበት ስለነበረ ነው። ሁለተኛው፣ ባለጌ የነበረው የገሊላው ገዢ የሄሮድስ የልደት በዓል ሲሆን በበዓሉ ላይ ጨፍራ ላስደሰተችው ልጅ ሽልማት እንዲሆን ሲል የመጥምቁ ዮሐንስን አንገት አስቆርጧል። በሁለቱም ጊዜያት የተፈጸመው ነገር እንዴት የሚቀፍ ነው!—ማቴዎስ 14:6–11

ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ እዚህ ላይ ያተኮረው ከወትሮው ለየት ባሉ ሁለት የልደት በዓላት ላይ አይደለምን? አይደለም። የጥንቱ የአይሁዳውያን ታሪክ ጸሐፊ ጆሴፈስ በልደት በዓል ላይ እንዲህ ዓይነት ተግባር መፈጸም ያልተለመደ ድርጊት እንዳልነበረ ገልጿል። ለመዝናኛ ተብሎ በልደት በዓል ላይ ሰዎች ስለተገደሉባቸው ሌሎች የልደት በዓሎችም መዝ ግቧል።

ለምሳሌ አንዳንዶቹ ግድያዎች ኢየሩሳሌም በ70 እዘአ ስትጠፋ 1,000,000 ሰዎች ካለቁና 97,000 ሰዎች በሕይወት ከተማረኩ በኋላ የተፈጸሙ ናቸው። እነዚህ እስረኞች ወደ ሮም እየተጋዙ ሳሉ ሮማዊው ጄኔራል ቲቶ ምርኮኞቹን አይሁዳውያንን በቅርብ ወደምትገኘው የቂሣርያ ወደብ ወሰዳቸው።

ጆሴፈስ እንዲህ በማለት ጽፏል፦ “ቲቶ ቂሣርያ እያለ ከ2,500 በላይ የሚሆኑ እስረኞች ከአውሬዎች ጋር ታግለውና በእሳት ነደው እንዲሞቱ በማድረግ የወንድሙን የዶሚሺያን ልደት በታላቅ በዓል አክብሯል። ከዚያ በኋላ ፍንቄ በምትባለው የሮም ቅኝ ግዛት ውስጥ ትገኝ ወደነበረችው ወደ ቤርየትስ [ቤይሩት] ሄደ። እዚያም በአንድ ታላቅ ትርኢት ላይ ሌሎች ተጨማሪ እስረኞችን በመግደል የአባቱን ልደት አክብሯል።”—ዘ ጂዊሽ ዎር ጥራዝ 7፣ ገጽ 37፤ ጆሴፈስ፦ ዘ ኢሴንሻል ራይቲንግስ በተባለው መጽሐፍ ውስጥ በፖል ኤል ሜየር የተተረጎመ።

እንግዲያው ኢምፔራል ባይብል ዲክሽነሪ የተባለው የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት “በኋለኞቹ ዘመናት የነበሩት ዕብራውያን የልደት ቀን ማክበርን የጣዖት አምልኮ ክፍል እንደሆነ አድርገው ይመለከቱት ነበር። በልደት ቀኖች ላይ ተዘውትረው ሲፈጸሙ የተመለከቷቸው ድርጊቶች ለዚህ አስተሳሰባቸው በቂ መሠረት ሆኗቸዋል” ማለቱ አያስደንቅም።

ታማኞቹ የመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቀፋፊ ሆኖ የቀረበውንና ሮማውያን ደግሞ እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ ያከብሩት የነበረውን በዓል ለማክበር እንዳልፈለጉ ግልጽ ነው። ዛሬም እውነተኛ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ልደት በዓላት የተናገራቸው ታሪኮች ለትምህርታችን ከተጻፉልን ነገሮች መካከል መሆናቸውን ይገነዘባሉ። (ሮሜ 15:4) የልደት በዓላትን አያከብሩም፤ ምክንያቱም እንዲህ ዓይነት በዓላት ለአንድ ግለሰብ ሊሰጠው የማይገባውን ክብር ይሰጣሉ። ከሁሉም በላይ ደግሞ የይሖዋ አገልጋዮች መጽሐፍ ቅዱስ የልደት በዓልን በሚዘገንን መንገድ ማስቀመጡን በቸልታ አያልፉትም።

[በገጽ 25 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በቂሣርያ የሚገኝ የመታገያ ቦታ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ