የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w95 1/15 ገጽ 32
  • ትንሽ ግን ኃይለኛ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትንሽ ግን ኃይለኛ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
w95 1/15 ገጽ 32

ትንሽ ግን ኃይለኛ

ካናዳዊው ወጣት ሮበርት የሕይወቱን ዓላማ ለማወቅ አውሮፓን በመዞር ተቅበዘበዘ። ስለ ወደፊቱ ጊዜ በትካዜ እንዲዋጥ ያደረጉትን ብዙ ነገሮች ዓይቶ ነበር።

ሮበርት በስፔይን ሴቪል በተባለች ከተማ አንድ ካፊቴሪያ ውስጥ ሳለ በይሖዋ ምሥክሮች የታተመ አንድ ትራክት ተበረከተለት። መጀመሪያ ላይ ሮበርት ጥርጣሬ አድሮበት ነበር። “ሆኖም አነበብኩት” አለ። “ልገልጸው ባልችልም አንድ ትርጉም ያለው ነገር እንዳለበት ተሰማኝ። በጉዞዬ ወቅት የሰዎችን ጭንቀትና ውድቀት የሚጠቁሙ ብዙ ነገሮች አይቻለሁ፤ ነገሮችን የመለወጥ ችሎታ ስለሌለኝም በጣም ተበሳጭቼ ነበር። ትራክቱን ካነበብኩ በኋላ ‘ይህ “አዲስ ዓለም” መምጣት ይችል ይሆን?’ ስል አሰብኩ። ከዚያም ‘ምናልባት ይመጣ ይሆናል’ የሚል ሐሳብ አደረብኝ።”

ሮበርት አዲስ ተስፋ በመያዝ፤ ወደ ቤቱ ሲመለስ አንድ ሰው መጥቶ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያስረዳው እርዳታ በመጠየቅ በካናዳ ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቢሮ ጻፈ።

በአንደበት የሚነገሩ ቃላት ኃይለኛ መሆናቸው አሌ አይባልም። ሆኖም በጽሑፍ የታተሙ መልእክቶች ያላቸውን ኃይል በጭራሽ አቅልለህ አትመልከት። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ጽሑፎች ምንም ትንሽ ቢሆኑ በጣም ይስባሉ። ስለ ወደፊቱ ጊዜ እርግጠኛ ተስፋ በመስጠት አእም ሮንና ልብን ይነካሉ።—ዕብራውያን 4:12

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ