የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w95 7/1 ገጽ 32
  • “ከጤናማ አእምሮ ውጪ የሆነ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ከጤናማ አእምሮ ውጪ የሆነ”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
w95 7/1 ገጽ 32

“ከጤናማ አእምሮ ውጪ የሆነ”

“ጦርነቶች የሚጀምሩት በሰዎች አእምሮ ውስጥ ስለሆነ የሰላምን ጋሻ መገንባት ያለብንም በሰዎች አእምሮ ውስጥ ነው።” (የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት ቻርተር) ይህንን አባባል በአእምሮ በመያዝ ከ500 የሚበልጡ ሊቃውንት በ1993 በተደረገው የተባበሩት መንግሥታት የጦር መሣሪያ ቅነሳ ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተው እንዲህ ያሉትን ጋሻዎች በመገንባት ረገድ ሃይማኖቶች የሚጫወቱትን ሚና መርምረው ነበር።

ጆናታን ግራኖፍ ለዓለም ደህንነት የሚሟገቱ ጠበቆችን በመወከል ኮንፈረንሱን በሊቀ መንበርነት መርተው ነበር። በሰሜን አየርላንድ፣ በስሪ ላንካ፣ በመካከለኛው ምሥራቅና በህንድ ያሉትን ሃይማኖታዊ ግጭቶች እንደ ማስረጃነት በመጠቀም “በአሁኑ ጊዜ የተስፋፋው የሃይማኖትና የጎሳ ግጭት ከጥሩ ሥነ ምግባር በጣም የራቀ፣ እንዲያውም ከጤናማ አእምሮ ውጪ የሆነ ድርጊት ነው” በማለት ተናግረዋል። “እስካሁን በተደረጉ ጦርነቶችና በተፈጥሮ አደጋዎች የሞቱ ሰዎች አንድ ላይ ቢደመሩ በሃይማኖት ስም የተገደሉትን ሰዎች አያክሉም” የሚሉት የጆን ኬንዝ ጋልብሬት ቃላት በስብሰባው ወቅት መጠቀሳቸው ተገቢ ነበር።

ዶክተር ሴሽጊሪ ራኡ እንዲህ አሉ፦ “ሐኪሞች በሽተኞችን መፈወስ እንጂ በሽታን ማሰራጨት አይጠበቅባቸውም። ሃይማኖታዊ ልማዶች ለእርቅ የሚገፋፉ እንጂ በሰዎች መካከል ጥላቻንና ግጭቶችን ማሰራጨት አይገባቸውም። ሐቁን ስንመለከት ግን አብዛኛውን ጊዜ የሚከፋፍሉ ኃይሎች በመሆን ሠርተዋል፤ አሁንም እየሠሩ ነው።

ከጥቂት ዓመታት በፊት የለንደኑ ካቶሊክ ሔራልድ አስተማማኝ ሰላም ማግኘት የሚቻለው “በዛሬው ጊዜ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ጦርነትን በጋራ ማውገዝ የሚችሉ ከሆነ ነው” በማለት አትቷል። ነገር ግን ጋዜጣው በማከል “ይህ ደግሞ በፍጹም እንደማይሆን እናውቃለን” ብሏል። አንዲት የካቶሊክ መነኩሴ እንዲህ ብለው ለመናገር ተገፋፍተው ነበር፦ “ሁላችንም አንድ ቀን ጠዋት ከእንቅልፋችን ስንነሳ . . . ልክ እንደ ይሖዋ ምሥክሮች ሁለተኛ የጦር መሣሪያ አንጨብጥም ብለን ቁርጥ ውሳኔ ብናደርግ ይህች ዓለማችን እንዴት ከአሁኑ የተለየች ትሆን ነበር!”

[ምንጭ]

Tom Haley/Sipa Press

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ