ዓለምን የሚገዛው አምላክ ነውን?
ቀኑ እሁድ ጠዋት ነው። ከአልጋዎ ተነሱ፣ ልብስዎን ለበሱ፣ ቁርስዎን በሉና ወደ ቤተ ክርስቲያን እየተቻኮሉ ሄዱ። እዚያም አምላክ ተወዳዳሪ የሌለው የመጨረሻው የምድር ባለ ሥልጣን መሆኑን የሚገልጽ ስብከት አደመጡ። አምላክ ለሰዎች በጥልቅ እንደሚያስብ ተነገርዎት። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚጠቅስ መግለጫ ቀረበ። ጉልበት ሁሉ በታዛዥነት የሚንበረከክለት የነገሥታት ንጉሥ እንደሆነ አደመጡ።
ከቤተ ክርስቲያን ተመልሰው ቤትዎ እንደደረሱ ቴሌቪዥን ከፍተው ዜና ተመለከቱ። አሁን ደግሞ ስለ ረሃብ፣ ስለ ወንጀል፣ ስለ አደንዛዥ ዕፅ፣ ስለ ድህነት የሚገልጽ ዜና አደመጡ። በሽታና ሞት ያስከተሏቸውን አሳዛኝ ሁኔታዎች ተመለከቱ።
በቤተ ክርስቲያን ስለ ሰሟቸው ነገሮች በተለይም እዚያ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው ስለማያውቁ ነገሮች እያሰቡ መገረም ጀመሩ። አምላክ አፍቃሪና ሁሉን ማድረግ የሚያስችል ኃይል ያለው ከሆነ አሠቃቂ ነገሮች ለምን ኖሩ? ስለ ኢየሱስ ክርስቶስስ ምን ሊባል ይቻላል? ለመመሪያዎቹ በታዛዥነት ያልተንበረከኩ ብዙ ጉልበቶች መኖራቸው ግልጽ ነው።
[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
አምላክ ዓለምን እየገዛ ከሆነ እንዲህ ዓይነት ሥቃይና ብጥብጥ የኖረው ለምንድን ነው?
[ምንጭ]
Cover: NASA photo