የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w95 11/15 ገጽ 20
  • የመዋለድና የጦርነት ሴት አማልክት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመዋለድና የጦርነት ሴት አማልክት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
w95 11/15 ገጽ 20

የመዋለድና የጦርነት ሴት አማልክት

ሶርያ ውስጥ ኢብል በተባለው ቦታ አርኪኦሎጂያዊ ቁፋሮ በሚካሄድበት ወቅት ኢሽታር ተብላ የምትጠራው የባቢሎናውያን የመዋለድና የጦርነት አምላክ ምስል ተገኘ። ፓኦሎ ማቲ የተባሉ አርኪኦሎጂስት ምስሉን እንደዚህ በማለት ገልጸውታል፦ “ጥምጣም ያደረጉ ካህናት በአንድ የመለኮት ምስል ፊት ቆመው የሚያሳይ ክብ ቅርፅ ያለው የአምልኮ ምስል ነው። . . . የምስሉ ራስ ረጅምና ቀጭን ከሆነ ድጋፍ ጋር ተጣብቋል።”

ምስሉ በ18ኛው መቶ ዘመን ከዘአበ መጀመሪያ ላይ የነበረ ስለሆነ ግኝቱ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ነው። ማቲ እንደተናገሩት ይህ ምስል የኢሽታር አምልኮ የ2,000 ዓመት እድሜ እንዳለው “የማያዳግም ማረጋገጫ” ይሰጣል።

የኢሽታር አምልኮ የተጀመረው በባቢሎን ሲሆን በተከታዮቹ መቶ ዓመታት በመላው የሮማ ግዛት ተሰራጭቷል። እስራኤላውያን ማንኛውንም የሐሰት ሃይማኖት ርዝራዥ ከተስፋይቱ ምድር እንዲያስወግዱ ይሖዋ አዝዞ ነበር። ቢሆንም ይህንን ትእዛዝ ስላልተከተሉ የአስታሮት አምልኮ (ከኢሽታር ጋር የምትመሳሰል የከነዓናውያን ጣዖት) ወጥመድ ሆነባቸው።—ዘዳግም 7:2, 5፤ መሳፍንት 10:6

ምንም እንኳ ኢሽታርና እኩያዋ አስታሮት በአሁኑ ጊዜ ባይኖሩም መለያቸው የሆነው ብልግና እና ዓመፅ አሁንም በሰፊው አለ። ዘመናዊው ኅብረተሰብ እነዚህን የመዋለድና የጦርነት ሴት አማልክት ያመልኩ የነበሩ ሰዎች ከነበሩበት የጥንቱ ሥልጣኔ ምኑን ተለየው ብለን እንገረም ይሆናል።

[በገጽ 20 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ልጆችም ታኒት ለተባለች ጣዖት መሥዋዕት ሆነው ይቀርቡ ነበር

[ምንጭ]

Ralph Crane/Bardo Museum

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ